am_jer_tn/26/01.txt

30 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ይህ ቃል እንዲህ ሲል ከያህዌ ዘንድ መጣ",
"body": "ይህ ፈሊጥ የዋለው ከያህዌ ዘንድ ልዩ መልዕክት ለማስተዋወቅ ነው፡፡ በኤርምያስ 18፡1 ላይ የሚገኘው ተመሳሳይ ሀረግ እንዴት እንደ ተተረጎመ ተመልክተው እንደ አስፈላጊነቱ ለውጥ ያድርጉ፡፡ \"ይህ መልዕክት የመጣው ከያህዌ ዘንድ ነው፡፡ እርሱ እንዲህ አለ\" ወይም \"ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ ቃል እንዲህ ሲል ከያህዌ ዘንድ መጣ",
"body": "ያህዌ መልዕክቱን ለማን እንደ ሰጠ፣ ይህ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ይህ ቃል ወደ ኤርምያስ ከያህዌ ዘንድ እንዲህ ሲል መጣ\" ወይም \"ያህዌ ይህን መልዕክት ለኤርምያስ ተናገረ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የይሁዳ ከተሞች",
"body": "\"ከተሞች\" የሚለው ቃል በከተማዋ ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ \"ከይሁዳ ከተማ የመጡ ሰዎች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከነገርኩህ ቃል አንዳች አታጉድል!",
"body": "\"ከነገርኩህ አንዳች ነገር አታስቀር!\""
},
{
"title": "እያንንዱ ሰው ከክፉ መንገዱ ይመለሳል",
"body": "ያህዌ የአንድ ሰው የአኗኗር ስልት \"መንገድ\" እንደሆነ ወይም ሰውየው የሚጓዝበት ጎዳና እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ \"እያንዳንዱ ሰው ክፉ የአኗኗር መንገዱን ያቆማል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለዚህም ከማደርሰው ጥፋት እመለሳለሁ/ይቅር እላለሁ",
"body": "ይህ ሁኔታን መሰረት ያደረገ ጥፋት/ቅጣት ነው፡፡ ይሁዳ ንስሃ ከገባ፣ እግዚአብሔር ጥፋት አያደርስም ይልቁንም ያድናቸዋል፡፡ "
},
{
"title": "የልምምዶቻቸው ክፋት",
"body": "\"እነርሱ የሚኖሩበት ክፉ ምነገድ\" ወይም \"እነርሱ የሚያደረጓቸው ክፉ ነገሮች\" "
}
]