am_jer_tn/25/27.txt

26 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡",
"body": "ይህ ምንባብ የያህዌን እጀግ ከፍ ያለ ቁጣ፣ የአገራቱ ህዝቦች ከጽዋው እንዲጠጡ እንዳደረጋቸው በዘይቤ መግለጹን ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ ያህዌ… እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "
},
{
"title": "በመካከላችሁ ከምልከው ሰይፍ አስቀድሞ ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ሰይፍ\" የሚለው ቃል የሚወክለው ጦርነትን ነው፡፡ \"በመካከላችሁ እንዲደርስ ከምፈቅደው ጦርነቶቹ አስቀድሞ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእኔ ስም የተጠራችው ከተማ",
"body": "ይህ እየሩሳሌምን ሲያመለክት በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽም ይችላል፡፡ \"በስሜ የተጠራችው ከተማ\" ወይም \"በስሜ የጠራኋት እየሩሳሌም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እናም እናንተ ራሳችሁ ከቅጣት ነጻ መሆን ይገባችኋልን?",
"body": "ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ህዝቡን ለመገሰጽ እና እንደሚቀጣቸው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ \"ስለዚህም እናንተ ራሳችሁ ከቅጣት ነጻ እንሆናለን ብላችሁ ታስባላችሁ?\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ ሁሉ ሰይፍ እጠራለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ሰይፍ\" የሚለው ቃል የሚወክለው ጦርነትን ነው፡፡ ያህዌ በህዝቡ ላይ ጦርነት ማወጅን የተናገረው በእነርሱ ላይ ሰይፍ እንደሚጠራ አድርጎ ነው፡፡ \"እኔ በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ ሁሉ ጦርነት አውጃለሁ\" ወይም \"እኔ በምድሪቱ ነዋሪዎች ላይ ሁሉ ጦርነት አመጣለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]