am_jer_tn/25/17.txt

22 lines
2.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሀሳብ፡",
"body": "ይህ ምንባብ የያህዌን እጀግ ከፍ ያለ ቁጣ፣ የአገራቱ ህዝቦች ከጽዋው እንደ ጠጡ አድርጎ በዘይቤ መግለጹን ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ መላው አገራት … ከዚያ እንዲጠጡ አድርጌያለሁ",
"body": "\"አገራት\" የሚለው ቃል የሚወክለው የአገራቱን ህዝቦች ነው፡፡ \"እኔ የሁሉም አገር ሰዎች … ከጽዋው ወይኑን እንዲጠጡ አድርጌያለሁ\" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አስፈሪ የሆነ ነገር",
"body": "\"አስፈሪ\" የሚለው ቅጽል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ሰዎችን የሚያስፈራ ነገር\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ "
},
{
"title": "ለጥናቻ እና እርግማ የሚዳርግ ነገር",
"body": "\"ጥላቻ\" የሚለው ቃል የሚገልጸው ጠንካራ ነቀፌታን/ተቀባይነት ማጣትን የሚያመለክት ድምጽን ነው፡፡ \"ጥላቻ\" እና \"እርግማን\" የሚሉት ሁለቱም በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ \"ሰዎች የሚጠሉት እና የሚረግሙት ነገር\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ "
},
{
"title": "እነርሱ በዚህ በዛሬው ቀን እየሆኑ ናቸው",
"body": "ለዚህ ሀረግ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የኤርምያስ መጽሐፍ የተጻፈበትን ጊዜ እና ኤርምያስ ይህንን ትንቢት ከተናገረ በኋላ ያለውን ጥቂት ጊዜ ይመልከቱ፡፡ ወይም 2) ይህ ማለት ኤርምያስ እዚህ ስፍራ የተነበያቸው ነገሮች መሆን ጀምረዋል፡፡"
}
]