am_jer_tn/24/04.txt

34 lines
3.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ፣ \"ያህዌ",
"body": "ይህ ፈሊጥ የዋለው ከያህዌ ዘንድ የተለየ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ መልዕክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህ አለ፣ ‘ያህዌ\" ወይም \"ያህዌ ይህንን መልዕክት እንዲህ ሲል ተናገረኝ፡ ‘ያህዌ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የይሁዳን ስደት ለእነርሱ ጥቅም ስል እመለከታለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"መመልከት\" የሚለው ያህዌ ለእነርሱ ይጠነቀቃል የሚል ትርጉም አለው፡፡ \"እኔ ለተሰደዱት ይሁዳ በመልካም ጥንቃቄ አደርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልክ እንደ እነዚህ መልካም በለሶች",
"body": "መልካሞቹ በለሶች የሚወክሉ ወደ ከለዳዊያን ምድር በስደት የሄዱትን አይሁዶች ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ ዐይኖቼን ለመልካም በእነርሱ ላይ አደርጋለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ዐይኖቼን አደርጋለሁ\" ማለት እርሱ ያያቸዋል ማለት ነው፡፡ እነርሱን ማየት ለእነርሱ ጥንቃቄ ማድረግ ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ \"እኔ እባርካቸዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ መልሼ እሰበስባቸዋለሁ፣ አላፈርሳቸውም፡፡ እኔ እተክላቸዋለሁ፣ አልነቅላቸውም",
"body": "እነዚህ ሁለት ዘይቤዎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለተኛው የመጀመሪያውን ያጠናክራል፡፡ \"በከለዳዊያን አገር እንዲበለጽጉ እረዳቸዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ መልሼ እሰበስባቸዋለሁ፣ አላፈርሳቸውም፡፡",
"body": "ያህዌ ስለ ስደተኞቹ በመልካም መሬት ላይ እንደሚተክላቸው እንጂ እንደማይነቅላቸው ተክሎች አድርጎ ይናገራል፡፡ \"በምድሪቱ ላይ አንጻቸዋለሁ፣ እንጂ አላስወግዳቸውም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔን እንዲያውቁኝ ልብ እሰጣቸዋለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ልብ\" የሚለው የሚያመለክተው የእነርሱን ፍላጎቶች ነው፡፡ \"እኔን ማወቅ እንዲፈልጉ አደርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሙሉ ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ሙሉ ልባቸው\" የሚለው \"ሙሉ ለሙሉ\" ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ \"ሙሉ ለሙሉ ወደ እኔ ይመለሳሉ\" ወይም \"ያለመቆጠብ ወደ እኔ ይመለሳሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]