am_jer_tn/23/37.txt

38 lines
3.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሃሳብ፡",
"body": "ያህዌ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን መልዕክት ያጠናቅቃል፡፡"
},
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ከቁጥር 33-40 ድረስ \"ሸክም\" የሚለውን ቃል በመደጋገም የሚደረግ አገላለጽ አለ፡፡ አንዳንዴ \"መልዕክተኛ\" ማለት ሲሆን በሌላ ጊዜ \"ለመሸከም ከባድ የሆነ ሸክም\" ማለት ይሆናል፡፡ ከተቻለ ይህ የቃላት ድግግም አገላለጽ እንዳለ ሊጠበቅ ይገባዋል፡፡"
},
{
"title": "አንተ የምትናገረው ይህንን ነው ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"አንተ\" የሚለው ነጠላ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው ኤርምያስን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነገር ግን እንዲህ ብትሉ… ምክንያቱም እንዲህ ብላችኋል…እኔ በምልካችሁ ጊዜ… እንዲህ አትሉም… እናንተን አነሳለሁ… እጥላችኋለሁ… መሳለቂያ አደርጋችኋለሁ",
"body": "በእነዚህ ሁኔታዎች ሁሉ \"እናንተ\" የሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው ካህናትን እና ሀሰተኛ ነቢያትን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለዚህ፣ እነሆ",
"body": "\"ስለዚህ ተጠንቀቁ\" ይህ አንባቢው ቀጥሎ ለሚሆነው ልዩ ትኩረት እንዲሰጥ ያነቃዋል፡፡"
},
{
"title": "እኔ እናንተን አንስቼ ከእኔ አርቄ ልጥላችሁ ነው",
"body": "ያህዌ የሚናገረው እነዚህን ካህናት እና ሀሰተኛ ነቢያት እንደሚጣል እቃ እንደሚጥላቸው እና ሩቅ ስፍራ ወደ ስደት እንደሚጥላቸው ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ ለእናንተ የሰጠኋት ከተማ",
"body": "ይህ እየሩሳሌምን ያመለክታል፡፡"
},
{
"title": "የማይረሳ ዘላለማዊ ሀፍረት እና ስድብ አድረግባችኋለሁ ",
"body": "\"ለዘለዓለም በሚኖር በሀፍረት እሸፍናችኋለሁ፣ የማትረሱትን ስድብ አደርስባችኋለሁ\" ወይም \"ሰዎች ለዘለዓለም እንዲሳለቁባችሁ አደርጋለሁ፡፡ ሰዎች ውርደታችሁን በፍጹም አይረሱም፡፡\" \"ያህዌ የካህናቱን እና የሀሰተኛ ነቢያቱን ውርደት የሚናገረው ሀፍረትን እና ስድብን እንደ ልብስ በላያቸው እንደሚደርብ አድርጎ ነው፡፡"
},
{
"title": "ያ አይረሳም",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ያ ለዘለዓለም ይኖራል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]