am_jer_tn/23/28.txt

26 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሃሳብ፡",
"body": "ያህዌ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን እና በኤርምያስ 23፡40 ላይ የሚጨርሰውን መልዕክቱን ማድረሱን ይቀጥላል፡፡"
},
{
"title": "ገለባ ከፍሬ ጋር ምን ግንኙነት አለው?",
"body": "ገለባ ገበሬዎች ዋጋ ያለውን ፍሬ ከለዩ በኋላ የሚቀረው ዋጋ የሌለው አገዳ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ትኩረት የሚሰጠው በሀሰተኛ መልዕክት እና ከያህዌ ዘንድ በሆነው መልክት መሃል ያለውን ልዩነት ነው፡፡ \"ገለባ እና ፍሬ ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ሁለት ነገሮች ናቸው፡፡\" ወይም \"ጥቅም የሌለው ገለባ በፍጹም ዋጋ እንዳለው ፍሬ አይደለም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቃሌ እንደ እሳት አይደለምን?... አለትን ሰባብሮ እንደሚያደቅ መዶሻስ አይደለምን?",
"body": "ያህዌ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ቃሉ ከሰዎች ተራ ቃል እጅግ እንደሚበልጥ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ በዚህ መንገድ የእርሱ ቃል እንደ እሳት ወይም መዶሻ ነው፡፡ \"ቃሌ እንደ እሳት ሀያል ነው… ደግሞም አለትን ሰባበብሮ እንደሚያደቅ መዶሻ ሀይለኛ ነው፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ እቃወማለሁ",
"body": "\"እኔ ከዚህ በተቃራኒ ነኝ\""
},
{
"title": "ከሌላ ሰው ቃላት ይሰርቃሉ",
"body": "ይህ የሚያመለክተው ሀሰተኛ ነቢያት ሌቦች መሆናቸውን ነው፡፡ የራሳቸውን ሀሰተኛ መልዕክት ከማዘጋጀት እንኳን አልፈው እርስ በእርሳቸው መልዕክቶችን ያለፈቃድ እስኪሰራረቁ ድረስ እጅግ ክፉዎች ናቸው፡፡ "
}
]