am_jer_tn/23/16.txt

38 lines
3.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሃሳብ፡",
"body": "ኤርምያስ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን የያህዌ መልዕክት ማድረሱን ይቀጥላል፡፡"
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ ያህዌ እንዲህ ይላል",
"body": "ብዙውን ጊዜ አርምያስ እነዚህን ቃላት የሚጠቀመው ከያህዌ ዘንድ ጠቃሚ ሀሳብን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "
},
{
"title": "እነርሱ አሞኝተዋችኋል!",
"body": "\"ነቢያቱ እውነት ያልሆነውን ነገር እንድታምኑ አድርገዋል!\""
},
{
"title": "ከአይምሯቸው የፈለቀውን ቅዠት",
"body": "እዚህ ስፍራ \"አይምሮ\" የሚለው የሚያመለክተው የሀሰተኛ ነቢያትን ሀሳብ ነው፡፡ \"እነርሱ የሚገምቱት ቅዠት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከያህዌ አፍ ያልሆነ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"አፍ\" የሚያመለክተው ያህዌ የተናገረውን ነው፡፡ \"ያህዌ ያልተናገረው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ሳያቋርጡ ይናገራሉ",
"body": "\"ሳያቋርጡ\" የሚለው ቃል ይህ ሁሌም የሚናገሩት ነገር እንደሆነ አጋኖ በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእናንተ ላይ ጥፋት አይመጣም",
"body": "\"በእናንተ ላይ ምንም ክፉ ነገር አይደርስም\""
},
{
"title": "ነገር ግን በያህዌ ምክር ላይ ማን ተገኝቷል?የእርሱን ቃል ማን አይቷል ማንስ ሰምቷል? ለእርሱ ቃል ማን ልቡን ሰጥቶ ሰምቷል?",
"body": "እነዚህ ጥያቄዎች የዋሉት ካህናቱ እና ሀሰተኛ ነቢያቱ ያህዌን ባለመታዘዛቸው ለመገሰጽ ነው፡፡ \"ማንም ያህዌን አላማከረውም፡፡ ማንም ያህዌ የተናገረውን አልተረዳም፡፡ ማንም የያህዌን ትዕዘዞች አልታዘዘም፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለእርሱ ቃላት ትኩረት ስጡ፣ አድምጡም",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ነገር ይገልጻሉ፡፡ በአንድ ሀረግ ሊጠቃላሉ ይችላሉ፡፡ \"ሙሉ ለሙሉ ለቃሉን ታዘዙ\""
}
]