am_jer_tn/23/11.txt

34 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አያያዥ ሃሳብ፡",
"body": "ኤርምያስ ስለ ሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት በ23፡9 ላይ የጀመረውን የያህዌ መልዕክት ማድረሱን ይቀጥላል፡፡ "
},
{
"title": "ነቢያቱ እና ካህናቱ ተበክለዋል",
"body": "ውሃ በቆሻሻ እንደሚበከል ነቢያቱ እና ካህናቱ በኃጢአት ረክሰዋል፡፡ \"ነቢያቱ እና ካህናቱ ኃጢአተኞች ናቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ክፋታቸውን በቤቴ እንኳን አግኝቼዋለሁ!",
"body": "\"ክፋት\" የሚለው ረቂቅ ስም እንደ ድርጊት ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"በቤተ መቅደሴ ጭምር ክፉ ድርጊት እንደፈጸሙ አውቃለሁ!\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእኔ ቤት",
"body": "ይህ የሚያመለክተው በእየሩሳሌም የሚገኘውን ቤተ መቅደስ ነው"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "መንገዳቸው በጨለማ ውስጥ በድጣማ ስፍራ እንደመሄድ ይሆናል",
"body": "የድርጊታቸው አደገኛነት የተገለጸው በጨለማ በሚያድጥ የገደል ጠርዝ ተንሸራቶ እንደመውደቅ እና ራሳቸውን እንደመጉዳት ተደርጎ ነው፡፡ \"ድርጊቶቻቸው በሚያድጥ ስፍራ በጨለማ እንደመራመድ ያልተረጋጉ እና አደገኞች ናቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእነርሱ ላይ ጥፋት እልካለሁ",
"body": "ያህዌ ጥፋትን የሚገልጸው ካህናቱን እና ሀሰተኛ ነቢያቱን እንዲያጠቃ እንደሚልከው ጠላት አድርጎ ነው፡፡ \"ጥፋት እንዲሰርስባቸው አደርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቅጣት በሚደርስባቸው አመት",
"body": "\"የሚቀጡበት ጊዜ ሲመጣ\" ወይም \"እኔ እነርሱን የምቀጣበት ጊዜ ሲደርስ\""
}
]