am_jer_tn/23/09.txt

38 lines
3.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ከቁጥር 9-13 ድረስ ኤርምያስ የያህዌን መልዕክት ለሀሰተኛ ነቢያት እና ካህናት ያደርሳል፡፡ ኤርምያስ በቁጥር 9 ላይ ይናገራል፣ ነገር ግን በቁጥር 10 ላይ የሚገኘው ቃል የኤርምያስ ይሁን የያህዌ ግልጽ አይደለም፡፡"
},
{
"title": "ነቢያትን በሚመለከት፣ ልቤ በውስጤ ተሰብሯል፣ ደግሞም አጥንቶቼ ሁሉ ተንቀጥቅጠዋል",
"body": "ነቢዩ ልቡ እንደተሰበረ እና አጥንቶቹ እንደ ተንቀጠቀጡ የሚናገረው ከሀሰተኛ ነቢያት የተነሳ የሚደርስበትን ቅጣት በመፍራት ነው፡፡ \"ከሀሰተኛ ነቢያት የተነሳ በሚደርሰው ታላቅ ፍርሃት አድሮብኛል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልቤ በውስጤ ተሰበረ",
"body": "ፈሊጡ የሚናገረው ጥልቅ ሀዘንን ነው፡፡ \"በጣም አዝኛለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አጥንቶቼ ሁሉ ተንቀጠቀጡ",
"body": "እዚህ ስፍራ ምንቀጥቀጥ የተያያዘው ከፍርሃት ጋር ነው፡፡ \"በጣም ፈርቻለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደ ሰከረ ሰው ሆንኩ፣ ወይን ጠጅ እንደተሞላ ሰው ሆንኩ",
"body": "የሰከሩ/የጠጡ ሰዎች ራሳቸውን መቆጣጠር አይችሉም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ፣ ኤርምያስ የያህዌን ቅጣት ከመፍራት የተነሳ ራሱን መቆጣጠር ተስኖታል፡፡ \"እኔ እንደ ጠጣ ሰው ሆኛለሁ፣ ራሴን መቆጣጠር ተስኖኛል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድሪቱ በምንዝርና ተሞልታለች",
"body": "ምድሪቱ መያዣ ዕቃ ተደርጋ እና አመንዝሮች ደግሞ ዕቃውን ሙሉ ለሙሉ እንደሞሉ ቁሶች ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ ያም ማለት፣ በምድሪቱ የሚገኝ እያንዳንዱ ሰው ዘማዊ ሆኖ ሲገለጽ፣ ይህም በተራው በጣም ብዙ ሰዎች ዘማዊ እንደሆኑ አጋኖ ይገልጻል፡፡ (ግነት እና አጠቃላ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አመንዝሮች ",
"body": "እዚህ ስፍራ ይህ ቃል ምናልበት ሁለት ስሜቶች አሉት፡፡ በቀጥታ ሲተረጎም በአገሪቱ የሚገኙ ወንዶች በገዛ ሚስቶቻቸው ላይ አመንዝረውባቸዋል ማለት ሲሆን፣ በዘይቤያዊ ትርጉሙ ጣኦት ለማምለክ ሲሉ ያህዌን ተተውታል የሚል ትርጉምም አለው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድሪቱ ደረቀች",
"body": "አንዳንድ ዘመናዊ ቅጂዎች ይህንን የዕብራይስጥ ሀረግ \"ምድሪቱ አለቀሰች\" በማለት ይተረጉሙታል፡፡"
},
{
"title": "የእነዚህ ነቢያት መንገዶች ክፉ ናቸው",
"body": "የሀሰተኛ ነቢያት ክፉ ድርጊቶች የተገለጹት በክፉ መንገድ ላይ እንደተራመዱ ተደርጎ ነው፡፡ \"እነዚህ ነቢያት ክፉ የሆኑ ነገሮችን እያደረጉ ነው\" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]