am_jer_tn/23/07.txt

38 lines
3.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "እነዚህ ቁጥሮች ምንም እንኳን በኤርምያስ 16፡14-15 ላይ ከሚገኘው ጋር ፍጹም አንድ ባይሆኑም በጣም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ እነዚያ እንዴት እንደተተረጎሙ ያነጻጽሩ፡፡"
},
{
"title": "እዩ",
"body": "ይህ ቃል ቀጥሎ ለሚነገረው አስደናቂ መረጃ ትኩረት ለመስጠት የሚያነቃ ነው፡፡"
},
{
"title": "ቀናት እየመጡ ነው",
"body": "መጪው ጊዜ የተነገረው ወደ ተናጋሪው ወይም ወደ አድማጩ እንደሚመጣ አካል ተደርጎ ነው፡፡ \"ጊዜው ይመጣል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ ህያው እንደሆንኩ",
"body": "\"እኔ ያህዌ በእርግጥ ህያው እንደሆንኩ፡፡\" ሰዎች ይህንን አገላለጽ የሚጠቀሙት ቀጥሎ የሚናገሩት ነገር በእርግጥ እውነት መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጽኑ ቃል ኪዳን የማድረግ ምልክት ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 4፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡\"እኔ በእርግጥ በክብሬ እምላለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሚያመጣ እና የሚመልስ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ይሰጣሉ ደግሞም ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ \"የሚመልስ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት",
"body": "\"ቤት\" የሚለው ቃል በቤቱ ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"እስራኤል\" ወይም \"የእስራኤል መንግሥት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰሜናዊ ምድር እና እነርሱ የተሰደዱበት ምድር",
"body": "ይህ የሚያመለክተው አስሩ ሰሜናዊ የእስራኤል ነገዶች ምርኮኛ የሆኑበትን እና በአካባቢያቸው በሚገኙ አገራት ውስጥ የተበተኑበትን መንገድ ነው፡፡ "
},
{
"title": "ከዚያ በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ ",
"body": "ይህ እስራኤላውያን ከየት እንደ ተበተኑ ያመለክታል፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ከዚያ ዳግም በገዛ ምድራቸው ይኖራሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]