am_jer_tn/22/24.txt

30 lines
3.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እኔ ህያው እንደሆንኩ",
"body": "\"በእርግጥ እኔ ህያው እንደሆንኩ፡፡\"ያህዌ ይህንን አገላለጽ የተጠቀመው እርሱ ቀጥሎ የሚናገረው በእርግጥ እውነት ለመሆኑን ለማሳየት ነው\" ይህ ጸና መሃላ የሚደረግበት መንገድ ነው፡፡ \"እኔ በህያውነቴ እምላለሁ፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምንም እንኳን አንተ… የቀኝ እጄ ማህተም ብትሆንም",
"body": "ያህዌ ኢኮንያንን የእጁ ቀለበት ሊሆን ይችል እንደነበር ይነግረዋል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቀኝ እጄ ያለው ማህተም",
"body": "የቀለበት ማህተም አንድ ንጉሥ በመዛግብት ላይ የስልጣን ማህተሙን ለማሳረፍ ይገለገልበት ነበር፡፡ ስለዚህም የቀለበት ማህተም የአገዛዝ ስልጣንን ይወክላል፡፡ ቀኝ እጅም ደግሞ የመግዛት ስልጣንን ይወክላል፡፡ \"ንግሥናዬን ስልጣን የሚያመለክተው በቀኝ እጄ ያለው የቀለበት ማህተም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "እኔ እጥልሃለሁ",
"body": "\"እኔ ከእጄ እጥልሃለሁ\" ወይም \"እኔ በፍጥነት ከእጄ እጥልሃለሁ\"ህይወትህን ለሚፈልጓት አሳልፌ ሰጥቼሃለሁ\nይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ህይወትህን የሚፈልጓት እንዲማርኩህ አገርጋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ) \n"
},
{
"title": "ለ…እጅ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እጅ\" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚወክለው ሀይል እና ቁጥጥርን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ህይወትህ ለሚፈልጉ",
"body": "ይህ ሀረግ የሚወክለው አንድን ሰው ለመግደል መፈለግን ወይም መሞከርን ነው፡፡ ይህ ሀረግ በኤርምያስ 11፡21 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"አንተን ለመግደል የሚሞክሩ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]