am_jer_tn/22/22.txt

26 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ነፋስ እረኞችሽን ሁሉ ነድቶ ይወስዳቸዋል",
"body": "የህ ቃላትን በመደጋገም የሚደረግ ገለጻ ነው - ያህዌ \"እረኛ\" የሚለውን ሃሳብ በተለያዩ ሁለት መንገዶች ተጠቅሞበታል፡፡ እዚህ ስፍራ \"እረኞች\" የሚለው ለእየሩሳሌም መሪዎች የዋለ ዘይቤ ነው፣ እናም ነፋስ \"ነድቶ\" ይወስዳቸዋል፡፡ ነፋስ ያህዌን ይወክላል፡፡ \"እኔ መሪዎችሽን ነፋስ ነድቶ የወሰዳቸው ይመስል ጠርጌ እወስዳቸዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወደ ምርዶ ይወሰዳሉ",
"body": "\"ምርኮኛ ይሆናሉ\" ወይም \"በስደት ይሄዳሉ\""
},
{
"title": "አንተ በ‘ሊባኖስ' የኖርክ ቤትህን በጥድ ቤት የሰራህ",
"body": "ያህዌ ንጉሣዊውን ቤተመንግሥት እንደ ‘ሊባኖስ' እና ‘የጥድ ቤት' የገለጸው በብዙ ጥድ የተሰራ በመሆኑ ነው፡፡ \"አንተ በሊበሰኖስ ጥድ በተሰራ በቤተ መንግሥት የምትኖር\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ በ …የምትኖር",
"body": "ይህ \"አንተ\" የሚለው ተውላጠ ስም ነጠላ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው ንጉሡን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ እንዴት ታዝናለህ",
"body": "የዕብራይስጡ ትርጉም ግልጽ አይደለም፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) \"እነርሱ እጅግ ለአንተ ያዝናሉ\" ወይም 2) \"አንተ ታላቅ የጭንቀት ድምጽ ታሰማለህ፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በወሊድ ላይ እንደምትገኝ ሴት የምጥ ስቃይ ሲደርስብህ",
"body": "ጠላቶቹ ሲያሸንፉት ንጉሡ የሚሰማው ስቃይ ሴት ልጅ ስትወልድ እንደሚሰማት ስቃይ ጠንካራ ይሆናል፡፡ \"ሴት በምጥ ሰአት እንደሚደርስባት ያለ ስቃይ በሚደርስብህ ጊዜ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]