am_jer_tn/22/17.txt

26 lines
3.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ሌሎችን በማጥፋትህ… ከጭንቀት በስተቀር በዐይኖችህን እና በልብህ ምንም አይኖርም",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ዐይኖች\" የሚለው ማየት ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን \"ልብ\" የሚለው ለማሰብ ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ \"ሌሎችን ከማጥፋት … በስተቀር በፍጹም ምንም ነገር አታይም ወይም አታስብም\" ወይም \"የምትመለከተው እና የታስበው ሁሉ ሌሎችን ስለ ምታታልልበት መንገድ ንጹህ ደም የምታፈስበትን፣ ደግሞም ሌሎችን የምትጨቁንበትን እና የምታጠፋበትን መንገዶች ነው\" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ተገቢያልሆነ ትርፍ",
"body": "ይህ በማታለል ወይም ተገቢያልሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ገንዘብ ማግኘት ነው፡፡"
},
{
"title": "የንጹሃንን ድም ማፍሰስ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ድም…ማፍሰስ\" የሚለው የተያያዘው ከግድያ ጋር ነው፤ \"ደም\" የሚያመለክተው የተገደሉትን ሰዎች ነው፡፡ \"የዋህ ሰዎችን መግደል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ስኔክቲክ/የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሌሎችን ማጥፋት",
"body": "\"ገንዘብ ለማግኘት በሌሎች ላይ የሃይል ድርጊት መፈጸም\""
},
{
"title": "ለእርሱ አያለቅሱለትም",
"body": "በቁጥር 18 ላይ፣ ያህዌ በቀጥታ ለኢዮአቄም መናገሩን አቁሞ ለሌሎች ሰዎች መናገር ይጀምራል፡፡ እዚህ ስፍራ \"ለቅሶ\" የሚለው የሚያመለክተው በኢዮአቄም ሞት ማዘንን ነው፡፡ \"ኢዮአቄም በሚሞትበት ጊዜ አያለቅሱለትም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አህያ እንደሚቀበር ይቀበራል፤ ጎትተው አውትተው ይጥሉታል",
"body": "የኢዮአቄም ቀብር የተገለጸው ሰዎች አህያ በሚቀብሩበት መንገድ እንደሚደረግ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"በድኑን የአህያ በድን በሚቀብሩበት መንገድ ይቀብራሉ፤ እየጎተቱ ወስደው ይጥሉታል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]