am_jer_tn/21/11.txt

30 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የይሁዳን ንጉሥ ቤት በሚመለከት፣ የያህዌን ቃል አድምጡ",
"body": "ይህ ከኤርምያስ 21፡12-23 ድረስ ላለው ክፍል አርእስት ሆኖ ሊያገለግል ይችላል፡፡ \"ያህዌ ስለ ይሁዳ ንጉሥ፣ ስለ ቤተሰቡ እና ስለ አገልጋዮቹ የሚናገረውን አድምጡ\""
},
{
"title": "የይሁዳ ንጉሥ ቤት",
"body": "\"ቤት\" የሚለው ቃል በንጉሡ ቤት ለሚኖሩ ሰዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው ንጉሡን እና ቤተሰቡን ነው፡፡ \"የይሁዳ ንጉሥ እና ቤተሰቡ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "የዳዊት ቤት",
"body": "ይህ የሚያመለክተው \"በይሁዳ ንጉሥ ቤት\" እንደሚላቸውን ተመሳሳይ ሰዎች ነው፡፡ መላው የይሁዳ ነገሥታት የዳዊት ትውልድ ናቸው፡፡ \"የዳዊት ትውልዶች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "በማለዳ ፍትህ ይሆናል",
"body": "\"ፍትህ\" የሚለው ረቂቅ ስም ድርጊት ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ሁልጊዜም የምትገዟቸውን ሰዎች በትክክል አስተዳድሯቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የጨቋኝ እጅ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እጅ\" የሚወክለው ሀይልን ነው፡፡ \"እነርሱን የጨቆነው ሀይል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ቁጣዬ እንደ እሳት ወጥቶ ይነዳል",
"body": "እዚህ ስፍራ የያህዌ ቁጣ የተነገረው ክፉ የሰሩትን እንደሚያቃጥል አሳት ተደርጎ ነው፡፡ \"እናንተን በቁጣዬ በቶሎ አንዳችሁንም ሳላስቀር ቀጥቼ አጠፋችኋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ይህን ማስቀረት የሚችል የለም",
"body": "ኤርምያስ በተነጻጻሪ ዘይቤ የቀረበውን የያህዌን ቅጣት በውሃ ሊጠፋ እንደማይችል ታላቅ እሳት መግለጹን ቀጥሏል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]