am_jer_tn/18/21.txt

50 lines
5.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ልጆቻቸውን ለረሃብ አሳልፈህ ስጣቸው",
"body": "\"አሳልፈህ ስጣቸው\" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር አንድን ሰው በሌላው ሀይል ስር ማድረግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኤርምያስ ስለ \"ረሃብ/ችጋር\" የሚናገረው በሌላው ሰው ላይ ስልጣን እንዳለው ሰው አድርጎ ነው፡፡ \"ልጆቻቸው በረሃብ እንዲሞቱ አሳልፈህ ስጣቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰይፍ ለያዙ እጆች አሳልፈህ ስጣቸው",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እጆች\" የሚለው ቃል የሚወክለው ሀይልን ነው፡፡ \"ሰይፍ የያዙ በእነርሱ ላይ ሀይል እንዲኖራቸው አድርግ\" ወይም \"በጦር ሜዳ ይሙቱ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሴቶቻቸው ሀዘንተኞች እና መበለቶች ይሁኑ",
"body": "\"የሴቶቻቸው ባሎች እና ልጆቻቸው ይሙቱ፡፡ \"ሀዘንተኞች\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ልጆቻቸው የሞቱባቸውን ሴቶች ነው፡፡ "
},
{
"title": "ወንዶቻቸው ይገደሉ",
"body": "ምናልባት ግሡ ከቀደመው ሀረግ ሊገኝ ይችላል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ሰዎች ወንዶቻቸውን ይግደሏቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወጣት ወንዶቻቸው በጦርነት በሰይፍ ይገደሉ",
"body": "ምናልባት ግሡ ከቀደመው ሀረግ ሊገኝ ይችላል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ሰዎች ወጣት ወንዶቻቸውን በጦር ሜዳ በሰይፍ ይግደሏቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የጥፋት ጩኸት ይሰማ",
"body": "\"የጥፋት ጩኸት\" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ሰዎች የጭንቀት ጨኸትን ይስሙ\" ወይም \"ሰዎች የሌሎችን የጭንቀት ጩኸት ይስሙ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "እኔን ለማጥመድ ጉድጓድ ቆፍረዋል፣ ለእግሬም ወጥመድ አበጅተዋል ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ኤርምያስ ጠላቶቹ እርሱን ለመግደል እያቀዱ መሆኑን የገለጸው የሚወድቅበትን ጉድጓድ እንደቆፈሩ እና እርሱን ለማጥመድ ወጥመድ እንዳዘጋጁ አድርጎ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ጉድጓድ ቆፍረዋል",
"body": "ይህ በኤርምያስ 18፡20 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "
},
{
"title": "ለእግሬ ወጥመድ አዘጋጅተዋል",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እግር\" የሚለው ቃል የሚወክለው ኤርምያስን ነው፡፡ \"ለእኔ ወጥመድ አዘጋግተዋል/አጥምደዋል\" ወይም \"ውድቀቴን ለማፍጠን ወጥመድ አጥምደዋል\" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ኃጢአታቸውን ከአንተ ዘንድ አትደምስስላቸው",
"body": "ኤርምያስ ያህዌ የእርሱን ጠላቶች ኃጢአት ይቅር ማለቱን አንድ ሰው የእነርሱን ኃጢአት እንደመዘገበ እና ያህዌ ይንን እንደሚያጠፋው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ የዚህ ሀረግ ትርጉም ከቀደመው ሀረግ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ \"ኃጢአታቸውን ይቅር አትበል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከአንተ ፊት የተጣሉ ይሁኑ",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ሰዎች በፊትህ የተጣሉ ያድርጓቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቁጣህ ቀን",
"body": "\"ቁጣ\" የሚለው ቃል በግስ መልኩ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"አንተ በእነርሱ ላይ ተቆጥተህ ሳለ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]