am_jer_tn/18/15.txt

34 lines
3.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በመንገዶቻቸው እንዲደነቃቀፉ ይሆናሉ",
"body": "ያህዌ የአንድን ሰው የህይወት ዘይቤ እንደሚሄድበት መንገድ አድርጎ ሲናገር፣ ለእርሱ ታማኝ ያልሆነ ሰው በመንገዱ ላይ እየተደነቃቀፈ እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ይህ በመንገዳቸው እንዲደነቃቀፉ ያደርጋል\" ወይም \"ይህ በመንገዳቸው እንዲደነቃቀፉ ያደርጋል\" ወይም \"ይህ በመንገድ ላይ ሲራመዱ እንደሚደነቃቀፉ ያለ ይሆናል\" (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዝቅ ባለ መንገድ ለመሄድ የጥንቶቹን መንገዶች ተዉ",
"body": "ያህዌ የአንድን ሰው የህይወት ዘይቤ እንደሚሄድበት መንገድ አድርጎ ይናገራል፡፡ እዚህ ስፍራ \"የጥንቶቹ መንገዶች\" የሚለው የሚወክለው ያህዌ አባቶቻቸው እንዲኖሩበት የነገራቸውን መንገድ ሲሆን \"አነስተኛ/ዝቅ ያሉ መንገዶች\" የሚለው ደግሞ የሚወክለው ለያህዌ በታማኝነት አለመኖርን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አስፈሪ ሆኑ",
"body": "\"አስፈሪ\" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ሰዎችን የሚያስፈራ ነገር ይሆናል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዘለዓለማዊ የጥላች ድምጽ አካል",
"body": "\"የጥላች ድምጽ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ጠንካራ የሆነ ያለ መቀበልን መግለጫ ድምጽ ሲሆን በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ሰዎች ሁሌም የጥላቻ ድምጽ የሚያሰሙበት ነገር\""
},
{
"title": "በአጠገቧ ሲያልፉ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እርሷ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምድራቸውን ነው፡፡"
},
{
"title": "በጠላቶቻቸው ፊት እንደ ምስራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ ",
"body": "ያህዌ ህዝቡን፣ አብዋራን እና ፍርስራሽን እንደሚበትን የምስራቅ ነፋስ ሆኖ በጠላቶቻቸው ፊት እንደሚያሳድዳቸው ይናገራል፡፡ \"እንደ ምስራቅ ነፋስ ሆኜ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ\" ወይም \"የምስራቅ ነፋስ አብዋራን እና ፍርስራሽን እንደሚበትን በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱን እበትናለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እነርሱ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው \"የእኔ ህዝብ/ህዝቤ\" የሚለውን ነው፡፡"
},
{
"title": "ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አያዩም",
"body": "\"በእነርሱ ላይ ጀርባዬን አዞራለሁ፣ እንጂ ፊቴን አያዩም፡፡\" በአንድ ሰው ላይ ጀርባን ማዞር አለመቀበልን የሚያመለክት ሲሆን ወደ አንድ ሰው ፊትን መመለስ መቀበልን/ሞገስ ማግኘትን የሚያመለክት ተምሳሌታዊ ድርጊት ነው፡፡ \"እኔ አልቀበላቸውም ለእነርሱ ሞገስ አልሰጥም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]