am_jer_tn/18/13.txt

22 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እንደዚያ ያለ ነገር የሰማ ህዝብ ይኖር እንደሆነ ጠይቁ?",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ህዝብ\" የሚለው ቃል የሚወክለው በአገራት ውስጥ የሚገኙ ሰዎችን ነው፡፡ ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው የይሁዳን ህዝብ ለመገሰጽ ነው፡፡ \"አንዳቸውም እንዲህ ያለ ነገር ሰምተው ያውቁ እንደሆነ እስቲ አገራትን ጠይቁ፡፡\" ወይም \"በምድር ላይ በየትኛውም ስፍራ ማንም እንዲህ ያለ ነገር ሰምቶ አያውቅም፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድንግሊቱ እስራኤል አሰቃቂ ድርጊት ፈጸመች",
"body": "አገራትን በሴት መግለጽ የተለመደ ነበር፡፡ ያህዌ እስራኤልን ለእርሱ ንጽህት እና ታማኝ እንደሆነች ሲገልጽ ድንግል እንደሆነች አድርጎ ሲሆን የእስራኤልን ለእርሱ ታማኝ አለመሆን የሚገልጸው \"አሰቃቂ ድርጊት እንደፈጸመች\" በማድረግ ነበር፡፡ \"እንደ ድንግል የሆነችው እስራኤል፣ አሰቃቂ ድርጊት ፈጸመች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ዘይቤያው አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሊባኖስ ተራራ አለታማ ኮረብቶች በረዶ ተለይቷቸው ያውቃልን?",
"body": "ያህዌ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው በተራሮቹ ላይ የሚገኘው በረዶ እንደማይቀልጥ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ \"በሊባኖስ የሚገኘው በረዶ በጎኖቹ የሚገኙትን አለታማ ኮረብቶች ተለይቶ አያወቅም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በጎኖቹ የሚገኙ አለታማ ኮረብቶች ",
"body": "\"የአለታማ ኮረብቶች ተረተር/ጎኖች\""
},
{
"title": "ከተራራ የሚወርዱ፣ ከርቀት የሚመጡ እነዚያ ቀዝቃዛ ምንጮች ሊጠፉ ይችላሉን?",
"body": "ያህዌ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚያነሳው የተራራ ምንጮች መፍሰሳቸውን በፍጹም እንደማያቋርጡ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ ምንጮቹ የሚደርቁት ከጠፉ እንደሆነ ይናገራል፡፡ \"ከርቀት የሚመጡት እነዚያ ቀዝቃዛ የተራራ ምንጮች መፍሰሳቸውን በፍጹም አያቆሙም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]