am_jer_tn/18/11.txt

34 lines
3.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እዩ/እነሆ",
"body": "ይህ አንባቢው ቀጥሎ ለሚሆነው ትኩረት እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ \"ተመልከቱ\" ወይም \"አድምጡ\" ወይም \"ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ\""
},
{
"title": "በእናንተ ላይ ጥፋት ለማድረስ ተነስቻለሁ፡፡ በእናንተ ላይ የጥፋት እቅድ አዘጋጅቻለሁ",
"body": "ያህዌ ጥፋት ሊያመጣ መነሳቱን የገለጸው ሸክላ ሰሪው ሸክላ እንደሚያበጅ ጥፋት እርሱ የሚያበጀው አካል እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ ሁለተኛው ዐረፍተ ነገር የመጀመሪያው የተለያዩ ቃላትን እንደተጠቀመ ሁሉ ተመሳሳይ ሃሳብን ይደግማል፡፡ \"እኔ በእናንተ ላይ ጥፋት ለማምጣት ተነስቻለሁ/እቅድ አድርጌያለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እቅድ ማዘጋጀት",
"body": "\"እቅድ ማውጣት\""
},
{
"title": "የእርሱ ክፉ መንገድ",
"body": "ያህዌ የአንድን ሰው የህይወት ዘይቤ የዚያ ሰው \"መንገድ\" ወይም የሚሄድበት መንገድ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ \"ክፉ የህይወት መንገዱ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለዚህ የእናንተ መንገዶች እና ልምምዶቻችሁ መልካም ነገር ያመጡላችኋል",
"body": "\"መንገዶች\" እና \"ልምምዶች\" የሚሉት ቃላት ሁለቱም የአንድን ሰው ድርጊቶች እና አጠቃላይ የህይወት ዘይቤ ያመለክታሉ፡፡ \"ስለዚህ ድርጊቶቻችሁ መልካም እንዲሆንላችሁ ያደርጋሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነገር ግን እነርሱ እንዲህ ይላሉ",
"body": "\"እነርሱ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የይሁዳን እና የእየሩሳሌምን ነዋሪዎች ነው፡፡ "
},
{
"title": "ይህ ጥቅም የለውም",
"body": "ለዚህ ፈሊጥ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ህዝቡ ኤርምያስ ለሚነግራቸው ጥንቃቄ አያደርጉም/ደንታ ቢስ ናቸው፡፡ \"አንተ ለምትናገረው ግድ የለንም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) ህዝቡ ኤርምያስ የሚናገራቸውን በማድረግ መልካም እንደሚሆን አያስቡም፡፡ \"የምተናገረው የሚሆን ነገር አይደለም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእርሱ ክፉ፣ እና ግትር ልብ የሚፈልገው",
"body": "\"ልብ\" የሚለው ቃል የሚወክለው የሰውየውን አይምሮ እና ፈቃድ ነው፡፡ \"የእርሱ ክፉ፣ እና ግትር አይምሮ/አስተሳሰብ የሚፈልገው\" ወይም \"በግትርነት ማድረግ የምንፈልገው ማናቸውም አይነት ክፉ ነገሮች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]