am_jer_tn/18/09.txt

14 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እገነባታለሁ ወይም እተክላታለሁ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ያህዌ መንግሥታትን ስለ ማጠናከር የሚናገረው እርሱ እንደሚገነባቸው ህንጻዎች፣ እና እንደሚተክላቸው ተክሎች አድርጎ ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእኔ ዐይኖች ፊት እርሷ ክፉ ብታደርግ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እርሷ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው አገሪቱን ወይም መንግሥቷን ነው፣ ይህም በዚያች አገር ለሚኖሩ ሰዎች ወይም መንግሥት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ \"ዐይኖች\" የሚለው ቃል የሚወክለው ማየትን ሲሆን፣ ማየት ደግሞ ሀሳብን ወይም ፍርድን ይወክላል፡፡ \"የዚያች አገር ሰዎች እኔ ክፉ ነው የምላቸውን ነገሮች ቢያደርጉ \" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድምጼን ባትሰሙ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ድምጽ\" የሚለው ቃል የሚወክለው የያህዌን ንግግር ነው፡፡ እዚህ ስፍራ፣ \"አለ መስማት\" አለመታዘዛቸውን የሚያሳይ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ \"ለነገርኳችሁ ባትታዘዙ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]