am_jer_tn/18/05.txt

34 lines
3.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከያህዌ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል የመጣ ቃል፣ \"መናገር አለብህ\"",
"body": "ይህ ፈሊጥ የዋለው ከእግዚአብሔር ልዩ መልዕክት ለማምጣት ነው፡፡ ተመሳሳይ የሆነው ሀረግ በኤርምያስ 1፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ መልዕክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህ አለ፣ 'መናገር አለብህ\" ወይም \"ያህዌ ይህን መልዕክት ለእኔ ተናገረ፡ 'መናገር አለብህ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት ሆይ እኔ በእናነተ ላይ እንደዚህ ሸክላ ሰሪ ማድረግ አልችልምን?",
"body": "በዚህ ጥያቄ ያህዌ በእስራኤል ላይ ደስ የሚያሰኘውን ለማድረግ ስልጣን እንዳለው ትኩረት ይሰጣል፡፡ \"የእስራኤል ቤት ሆይ፣ ሸክላ ሰሪው በሚሰራው ሸክላ ላይ ስልጣን እንዳለው እኔ በእናንተ ላይ ማድረግ እችላለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት",
"body": "\"ቤት\" የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩ ቤተሰቦች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ይህ የሚያመለክተው የእስራኤልን መንግሥት ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"እስራኤል\" ወይም \"የእስራኤል መንግሥት\" ወይም \"የእስራኤል ህዝብ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነሆ",
"body": "\"የምናገረው እውነተኛ እና ጠቃሚ ስለሆነ ትኩረት ሰጥተህ ስማ\""
},
{
"title": "በሸክላ ሰሪው እጅ እንደሚገኝ ጭቃ - እናንተ በእኔ እጅ እንደዚያ ናችሁ",
"body": "ሸክላ ሰሪው ይሆናል በሚለው መንገድ በእጁ ያለውን ጭቃ ዳግም መስራት እንደሚችል ያህዌ አስራኤልን ዳግም መስራት እንደሚችል ያነጻጽራል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይንደዋል፣ ወይም ያፈርሰዋል",
"body": "እነዚህ ሁለት አገላለጾች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በመጀመሪያው ገለጻ፣ ያህዌ አንድን መንግሥት ያ መንግሥት ተክል እንደሆነ ወይም የሚያፈርሰው ህንጻ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይቅር እላለሁ",
"body": "\"አስቀርለታለሁ\" ወይም \"አላመጣበትም\""
}
]