am_jer_tn/18/01.txt

34 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከያህዌ ወደ ኤርምያስ እንዲህ ሲል የመጣ ቃል፣ \"ተነስ\"",
"body": "ይህ ፈሊጥ የዋለው ከእግዚአብሔር ልዩ መልዕክት ለማምጣት ነው፡፡ ተመሳሳይ የሆነው ሀረግ በኤርምያስ 7፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ለኤርምያስ የሰጠው መልዕክት ይህ ነው፡፡ እንዲህ አለ፣ 'ተነስ\" ወይም \"ያህዌ ለኤርምያስ የተናገረው መልዕክት ይህ ነው፡ 'ተነስ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሸክላ ሰሪው ቤት",
"body": "\"የሸክላ ሰሪው የስራ ስፍራ፡፡\" ሸክላ ሰሪ ከጭቃ ሸክላ የሚሰራ ሰው ነው፡፡"
},
{
"title": "እነሆ!",
"body": "\"እነሆ\" የሚለው ቃል በታሪኩ ውስጥ አዲስ ሰው እንደሚገባ ያነቃናል፡፡ የእናንተ ቋንቋ ለዚህ የራሱ የሆነ አገላለጽ ሊኖረው ይችላል፡፡"
},
{
"title": "በሸክላ ሰሪው መንኮራኩር",
"body": "የሸክላ ሰሪው መንኮራኩር የሚሽከረከር ትንሽ ጠረጴዛ ነው፡፡"
},
{
"title": "የሚሰራው ጭቃ በእጁ ላይ ተበላሸ",
"body": "\"ተበላሸ\" የሚለው ቃል የሚሰራው ቁስ ብልሽት አለበት ማለት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"በእጁ ላይ የነበረው የሚያበጀመው የሸክላ እቃ ጥሩ አልነበረም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ያበጀው የነበረው",
"body": "\"ይሰራው የነበረው\" ወይም \"ቅርጽ ይሰጠው የነበረው\""
},
{
"title": "ስለዚህም ሀሳቡን ቀየረ",
"body": "የዚህ ፈሊጥ ትርጉም ሌላ ነገር ለመስራት መወሰን ማለት ነው፡፡ \"ስለዚህ የተለየ ምርጫ አደረገ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእርሱ ዐይኖች ለማድረግ መልካም ሆኖ የታየውን",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ዐይኖች\" የሚለው የሚወክለው ማየትን ሲሆን ማየት ደግሞ የሚገልጸው አስተያየትን/ሃሳብን ነው፡፡ \"ለማድረግ መልካም ሆኖ እንዳሰበው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]