am_jer_tn/17/17.txt

22 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አንተ የእኔ መሸሸጊያ ነህ",
"body": "ኤርምያስ ያህዌን ጠላቶቹ እርሱን ሊያጠቁት የማይችሉበት ስፍራ አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በመከራ ቀን ",
"body": "\"በመከራ ጊዜያት\""
},
{
"title": "አሳዳጆቼ ይፈሩ፣ እኔ እንዳፍር ግን አታድርግ",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"በአሳዳጆቼ ላይ እፍረት አምጣባቸው፣ በእኔ ላይ ግን ሀፍረት አታድርስ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ይጨነቁ፣ እኔን ግን እንድጨነቅ አታድርግ",
"body": "ይህ ሀረግ በመሰረቱ ከቀደመው ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፤ ደግሞም በኤርምያስ ጸሎት ላይ ትኩረት ይጨምራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"እጅግ አስፈራቸው፣ እኔን ግን እንድፈራ አታድርገኝ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእጥፍ መጠን ጥፋት ሰባብራቸው",
"body": "ኤርምያስ ያህዌ ጠላቶቹን እንደ ዕቃ እንዲሰባብራቸው ይናገራል፡፡ \"እጥፍ መጠን\" የሚለው ፈሊጥ ሁለቴ ያህል ማድረግ የሚል ትርጉም አለው፡፡ \"በሙሉ ጥፋት ሰባብራቸው\" ወይም \"ሁለቴ ያህል አጥፋቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ፈሊጥ የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]