am_jer_tn/17/15.txt

34 lines
2.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ተመልከት",
"body": "\"እይ\" ወይም \"አድምጥ\" ወይም \"ልነግርህ ለተዘጋጀሁት ትኩረት ስጥ\""
},
{
"title": "እነርሱ እኔን እንዲህ ይሉኛል",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እኔ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኤርምያስን ሲሆን \"እነርሱ\" የሚለው ጠላቶቹን ያመለክታል፡፡"
},
{
"title": "የያህዌ ቃል ወዴት አለ?",
"body": "ሰዎቹ ይህንን ጥያቄ ያነሱት/የተጠቀሙበት በኤርምያስ ላይ ለመሳለቅ ነው፤ ምክንያቱም የተናገራቸው ነገሮች ገና አልተፈጸሙም ነበር፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር መልክም ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ያህዌ የነገረህ ነገሮች መች ተፈጸሙ\" ወይም \"ያህዌ ይሆናሉ ብሎ የነገረህ ነገሮች አልተፈጸሙም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ ይምጣ",
"body": "\"ያህዌ የተናገረው ይሁን\""
},
{
"title": "አንተን በመከተል እረኛ ከመሆን አልሸሽም",
"body": "ኤርምያስ ህዝቡን መምራትን እና መሸከምን የሚገልጸው ራሱን በጎችን እንደሚሸከም እረኛ አድርጎ ነው፡፡ ያንን ስራ መተውን የሚገልጸው ከስራው እንደመሸሽ አድርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ አልመኘውም",
"body": "\"እኔ አልፈልገውም\""
},
{
"title": "ከከንፈሮቼ የወጡ ትዕዛዛት/ቃላት",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ከንፈሮች\" የሚለው ቃል የሚወክለው ተናገሪውን ኤርምያስን ነው፡፡ \"ትዕዛዝ/ቃል\" የሚለው በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"የተናገርኩት አዋጅ\" ወይም \"እኔ ያወጅኳቸው/የተናገርኳቸው ነገሮች\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ተደርገዋል",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"እኔ አደረግኳቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]