am_jer_tn/17/05.txt

22 lines
1.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በሰው ልጅ ላይ የሚታመን የተረገመ ነው",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"እኔ በሰው ልጅ ላይ የሚታመንን ማንኛውንም ሰው ረግመዋለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሱ ስጋን ሀይሉ ያደርጋል",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ስጋ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰው ልጅን/ሰዎችን ነው፡፡ \"እርሱ ለጥንካሬው በሰው ላይ ይታመናል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልቡን ከያህዌ ዞር ያደርጋል",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ልብ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሀሳብን እና ስሜትን ነው፡፡ \"መሰጠቱን/ጥሞናውን ከያህዌ ያርቃል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደ ትንሽ ቁጥቋጦ",
"body": "ከያህዌ ይልቅ በሰው የሚታመን ሰው ለም ባልሆነ መሬት ላይ ለማደግ እንደሚታገል ተክል ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰው የማይኖርበት፣ ምድረ በዳ እና ጠፍ ምድር",
"body": "\"ሰው የማይኖርበት ጠፍ ምድር\" የሚለው \"ምድረበዳ\" ከሚለው ጋር በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ \"ጠፍ ምድረ በዳ ማንም የማይኖርበት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]