am_jer_tn/17/01.txt

26 lines
2.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡",
"body": "ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ ትንቢት የሚጽፈው በግጥም መልክ ነው፡፡ የዕብራውያን ስነግጥም የተለያዩ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤዎችን ይጠቀማል፡፡ (ስነግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የይሁዳ ኃጢአት… በመሰዊያዎቻችሁ ቀንዶች ላይ ተጽፏል",
"body": "ያህዌ ስለ ይሁዳ ኃጢአት እጅግ ታላቅ መሆን አንድ ሰው ኃጢአታቸውን በቋሚነት እንደቀረጸው እና እነርሱም ሊያቆሙት እንደማይችሉ አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የይሁዳ ኃጢአት ተጽፏል",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ይሁዳ\" የሚለው ቃል የሚወክለው የይሁዳን ሰዎች ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"የይሁዳ ኃጢአት ተጽፏል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተቀርጽዋል",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ይህ ተቀርጽዋል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በልባቸው ጽላት ላይ ተቀርጽዋል",
"body": "የህዝቡ ኃጢአተኝነት ልምዶች የተገለጸው በየራሳቸው ልቦች ላይ እንደተቀረጸ ተደርጎ ነው፡፡ \"ልቦች\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሰውን ሁለንተና፡ ማለትም ሀሳብ፣ ስሜት እና ድርጊቶች ነው፡፡ \"በማንነታቸው ላይ ተቀርጽዋል\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በመሰዊያዎቻችሁ ቀንዶች ላይ",
"body": "\"ቀንዶች\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው በመሰዊያዎች ጠርዝ የሚገኙትን ጉጦች ነው፡፡ "
}
]