am_jer_tn/16/19.txt

46 lines
5.0 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ያህዌ፣ አንተ ጠንካራ ምሽጌ ነህ",
"body": "እዚህ ስፍራ ኤርምያስ ለያህዌ መናገር ይጀምራል፡፡"
},
{
"title": "ምሽጌ እና መሸሸጊያዬ፣ የደህንነቴ ስፍራ",
"body": "ኤርምያስ ያህዌ ለእርሱ ጠላቶቹ ሊያጠቁት የማይችሉበት ስፍራ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ አንዱን ሃሰብ ሶስት ጊዜ ይደጋግማል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ጥንድ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ህዝቦች ወደ አንተ ይሄዳሉ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ህዝቦች\" የሚለው ቃል የሚወክለው የተለያዩ አገራት ሰዎችን ነው፡፡ \"የተለያዩ አገራት ሰዎች ወደ አንተ ይሄዳሉ\" ወይም \"የአገራት ሰዎች ወደ አንተ ይመጣሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ሄደ እና መጣ የሚሉት ቃላት አገባብ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የምድር ዳርቻ",
"body": "ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን በምድር ላይ ሩቅ የሆነው ስፍራ ማለት ነው፡፡ ሁለቱን ጫፎች በማመሳከር፣ በመሃል የሚገኙትን ስፍራዎች ሁሉ ያመለክታል፡፡ \"በምድር ሩቅ የሆነው ስፍራ\" ወይም \"በምድር በሁሉም ስፍራ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና (ሜሪዝም/ከዳር እስከ ዳር/ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አባቶቻችን የሚያታልሉትን ሀሰተኞች ወረሱ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ማታለል\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሀሰተኛ ጣዖቶች ነው፡፡ \"አባቶቻችን አንዳች የማይጠቅሙ ሀሰተኛ ጣዖቶችን ወረሱ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ሄደ እና መጣ የሚሉት ቃላት አገባብ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ባዶናቸው፤ ከእነርሱ አንዳች ጥቅም አይገኝም",
"body": "እዚህ ስፍራ \"የእነርሱ\" እና \"ከእነርሱ\" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት አባቶች ያምኑባቸውን ጣዖቶች ነው፡፡ ሁለቱ ሀረጋት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው፤ ሁለተኛው እንዴት \"ከንቱ እንደሆኑ ያብራራል\" (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰዎች ለራሳቸው አማልክትን ያበጃሉን? ነገር ግን እነርሱ አማልክት አይደሉም",
"body": "ሰዎች ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቁት ሰዎች ለራሳቸው አማልክት ሊያበጁ እንደማይችሉ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ሰዎች ለራሳቸው አማልክትን ሊያበጁ አይችሉም፡፡ ያበጇቸው ነገሮች አማልክት አይደሉም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለዚህ ያያሉ",
"body": "\"ስለዚህ፣ በእርግጥ፡፡\" እዚህ ስፍራ ያህዌ መናገር ይጀምራል፡፡ \"ያያሉ\" የሚለው ቃል ቀጥሎ ለሚሆነው ትኩረት ይሰጣል"
},
{
"title": "እነርሱ እንዲያውቁ አደርጋለሁ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እነርሱ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የአገሩን ሰዎች ነው፡፡ ያህዌ ይህንን ሀረግ የሚደግመው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡"
},
{
"title": "የእኔ እጅ እና የእኔ ሀይል",
"body": "እዚህ ስፍራ \"እጅ\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሀይልን እና ስልጣንን ነው፡፡ ሁለቱ ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ደግሞም ለያህዌ ታላቅ ሀይል ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ \"ታላቁ ሀይሌ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ጥንድ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስሜ ያህዌ እንደሆነ ያውቃሉ",
"body": "እዚህ ስፍራ \" ስም\" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የያህዌን ማንነት ነው፡፡ \"እኔ እውነተኛ አምላክ የሆንኩ ያህዌ እንደሆንኩ ያውቃሉ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]