am_jer_tn/16/16.txt

38 lines
4.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ብዙ አሳ አጥማዶችን እልካለሁ… እነርሱም ህዝቡን ያጠምዳሉ",
"body": "ያህዌ ህዝቡን የሚያጠቃውን እና የሚገድለውን የጠላትን ሰራዊት አሳ እንደሚይዙ አሳ አጥማጆች አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በመሃላቸው ሆነው እንዲያድኗቸው ብዙ አዳኞችን እልካለሁ",
"body": "ያህዌ ህዝቡን የሚያጠቃውን እና የሚገድለውን የጠላትን ሰራዊት እንስሳትን እንደሚየድኑ አዳኞች አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ዐይኖቼ በመንገዶቻቸው ሁሉ ላይ ነው",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ዐይን\" የሚለው ቃል የሚወክለው የሚያደርጉትን ሁሉ የሚመለከተውን ያህዌን ነው፡፡ \"የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ እመለከታለሁ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ ከእኔ ፊት መሰወር አይችሉም",
"body": "\"እነርሱ\" የሚለው ቃል ሰዎቹን ወይም ድርጊታቸውን ሊያመለክት ይችላል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"እነርሱ ከእኔ ሊሰወሩ/ሊደበቁ አይችሉም\" ወይም \"መንገዳቸውን ከእኔ ሊደብቁ አይችሉም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ክፋታቸው ከዐይኖቼ ፊት ሊሸሸጉ አይችሉም",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ዐይኖች\" የሚለው የሚወክለው ሁሉን የሚመለከተውን ያህዌን ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"ከእኔ ሊደበቁ አይችሉም\" ወይም \"መንገዳቸውን ከእኔ ሊደብቁ አይችሉም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምድሬን አርክሰዋል",
"body": "ያህዌ ህዝቡ ምድሪቱን እንዳረከሱ አድርጎ፣ በፊት ተቀባይነት ማጣቷን ይናገራል፡፡ \"የእነርሱ እርክሰት\" የሚሉት ቃላት በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ምድሬን ስላረከሷት\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለእነርሱ ስሜቶች ርስቴን በአስጸያፊ ጣኦቶቻቸው ስለሞሏት",
"body": "\"መሙላት\" የሚለው ፈሊጥ በምድሪቱ ላይ ብዙ ጣኦታትን አደረጉ ማለት ነው፡፡ \"ለእነርሱ ስሜቶች\" የሚሉት ቃላት በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"የእኔን ርስት በአስጸያፊ ጣኦቶቻቸው በመሙላታቸው ምክንያት\" ወይም \"አስጸያፊ ጣኦቶቻቸው ርስቴ ባለበት ስፍራ ሁሉ በመደረጋቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእኔ ርስት",
"body": "ያህዌ ምድሪቱ እንደ ቋሚ ሀብቱ አድርጎ የቆጠራት የእርሱ ርስት እንደሆነች አድርጎ ይናገራል፡፡ \"የእኔ ርስት የሆነችው ምድር\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]