am_jer_tn/16/07.txt

34 lines
3.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "በደረሰባቸው የሞት ሀዘን ማንም አንዳች ምግብ ለሀዘኑ እነርሱን ለማጽናናት አያካፍላቸው…ማንም ለአባቱ ወይም ለእናቱ የማጽናኛ ዋንጫ/ጽዋ አይስጥ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እግዚአብሔር በመሰረቱ ተመሳሳይ የሆኑትን ነገሮች ሁለቴ የተናገረው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ምግብ ወይም መይን ጠጅ ዘመድ ወደሞተባቸው ሰዎች መውሰድ የተለመደ ነበር፡፡ ያህዌ ከሰዎቹ ማጽናኛዎችን ሁሉ ያስወገደው በኃጢአታቸው ምክንያት ነበር፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማንም የማጽናኛ ዋንጫ/ጽዋ አይስጣቸው",
"body": "እዚህ ስፍራ \"ዋንጫ/ጽዋ\" የሚለው ቃል የሚወክለው ዋንጫው/ሲኒ በውስጡ የያዘውን መጠጥ ነው፡፡ \"ማንም የመጽናኛ መጠጥ አይስጣቸው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድግስ ቤት",
"body": "\"ሰዎች ግብዣ የሚያደርጉበት ቤት\""
},
{
"title": "የጭፍሮች አለቃ ያህዌ… እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ብዙውን ጊዜ እነዚህን ቃላት ከእግዚአብሔር ዘንድ መልዕክትን ሲያመጣ ለማስተዋወቅ ይጠቀምባቸዋል፡፡ ይህ በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "
},
{
"title": "እነሆ/እዩ",
"body": "\"ተመልከቱ\" ወይም \"አድምጡ\" ወይም \"ቀጥሎ ለምናገረው ትኩረት ስጡ\""
},
{
"title": "የእናንተ ዐይኖች እየተመለከቱ",
"body": "እዚህ ስፍራ \"የእናንተ\" የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም የእስራኤልን ሰዎች ነው፡፡ የፈሊጣዊ አነጋገሩ ትርጉም ያህዌ ይህን የሚያደርገው እነርሱ ማየት በሚችሉበት ስፍራ ነው፡፡ \"በእናንተ ፊት ለፊት\" ወይም \"እናንተ ማየት በምትችሉበት ስፍራ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም መልኮች እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእናንተ ቀናት/ዘመን",
"body": "የዚህ ፈሊጥ ትርጉም በእነርሱ የህይወት ዘመን ማለት ነው፡፡ \"በእናንተ የህይወት ዘመን\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሀሴት እና የደስታ ድምጽ ፣ የሙሽራውና የሙሽራቱ ድምጽ",
"body": "ይህ በኤርምያስ 7፡34 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "
}
]