am_jer_tn/16/05.txt

30 lines
3.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ \"…አታድርግ",
"body": "ይህ ፈሊጥ የዋለው ከያህዌ ዘንድ የመጣ ልዩ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ መልዕክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህም አለኝ፣ \"…አታድርግ\" ወይም \"ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረኝ/ያህዌ እንዲህ አለኝ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልቅሶ ባለበት ስፍራ",
"body": "\"ልቅሶ\" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ \"ሰዎች በሚያለቅሱበት ስፍራ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰላሜን ከዚህ ህዝብ ወስጃለሁ… ደግሞም የጸናውን ፍቅር እና ምህረት ",
"body": "ያህዌ ለህዝቡ ከእንግዲህ ሰላም፣ የጸና ፍቅር እና ምህረት እንዳሌለው የገለጸው እነዚህ ከእነርሱ እንደተወሰዱ ነገሮች አድርጎ ነው፡፡ \"ከእንግዲህ ለእነርሱ ሰላም አላደርግላቸውም… ወይም የጸና ፍቅር እና ምህረት አላደርግላቸውም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የያህዌ አዋጅ/ትዕዛዝ ነው",
"body": "ያህዌ ስለ ራሱ በስሙ የሚናገረው/የሚምለው የተናገረው ነገር እርግጠኛ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ ያዘዘው ይህንን ነው\" ወይም \"እኔ ያህዌ ያዘዝኩት ይህንን ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ ወይም ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ታላላቆችም ታናናሾችም ሁሉም…",
"body": "ይህ የሚያመለክተው ሁሉንም አይነት ሰው ሲሆን፣ የሰዎቹ ደረጃ የተገለጸው በመጠን ነው፡፡ \"ታላላቆችም ታናናሾችም\" ወይም \"ከደረጃቸው ባሻገር ብዙ ሰዎች፣…\" (ሜሪዝም/ከዳር እስከ ዳር/ከጽንፍ እስከ ጽንፍ)"
},
{
"title": "አይቀበሩም",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ማንም አይቀብራቸውም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማንም… ሰውነቱን የሚቧጥጥላቸው ወይም ፀጉሩን የሚላጭላቸው አይኖርም",
"body": "ራስን መቧጠጥ/መቁረጥ እና የራስ ፀጉርን መላጨት ከፍተኛ ሀዘንን የመግለጫ ምልክታዊ ድርጊቶች ነበሩ፤ በተለይም በጣም የሚወዱት ሰው ሲሞት ይህ ይደረግ ነበር፡፡ (ምልክታዊ/ትዕምርታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]