am_jer_tn/16/01.txt

22 lines
2.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የያህዌ ቃል እንዲህ ሲል ወደ እኔ መጣ \"…አታድርግ",
"body": "ይህ ፈሊጥ የዋለው ከያህዌ ዘንድ የመጣ ልዩ መልዕክትን ለማስተዋወቅ ነው፡፡ ይህ በኤርምያስ 1፡4 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ \"ያህዌ መልዕክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህም አለኝ፣ \"…አታድርግ\" ወይም \"ያህዌ ይህን መልዕክት ተናገረኝ/ያህዌ እንዲህ አለኝ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱ በበሽታ ይሞታሉ",
"body": "\"በሚገድል ክፉ በሽታ ይሞታሉ\""
},
{
"title": "አይለቀስላቸውም ወይም አይቀበሩም",
"body": "ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ማንም ሰው አያለቅስላቸውም ወይም ማንም አይቀብራቸውም\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በምድር ላይ እንደ ፍግ ይሆናሉ",
"body": "በምድሪቱ የተወለዱ ወንዶች እና ሴቶች ልጆች በምድር ላይ ከሚገኝ ፍግ ጋር የተነጻጸሩት አስጸያፊ እንደሚሆኑ እና ማንም እንደማይቀብራቸው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ተመሳሳዩ ሀረግ በኤርምያስ 8፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሰይፍ እና በረሃብ መጨረሻቸው ይሆናል",
"body": "\"መጨረሻቸው ይሆናል\" የሚለው ሀረግ ይሞታሉ የሚለው ቀለል ባለ መንገድ/በጨዋ አነጋገር የተገለጸበት ነው፡፡ \"ሰይፍ\" የሚለው ቃል የሚገልጸው በሰይፍ የሚዋጋን ሰራዊት ወታደሮች ነው፡፡ ሀረጉ በጦርነት ውስጥ መሞትን ይገልጻል፡፡ \"በጦርነት ውስጥ ወይም በረሃብ ይሞታሉ\" (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]