am_jer_tn/15/17.txt

22 lines
2.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ከ… ጋር አልተቀመጥኩም፡",
"body": "ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ \"እኔ ከ… ጋር ጊዜ አላጠፋሁም\" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከሀይለኛው እጅህ",
"body": "እዚህ ስፍራ የያህዌ \"ሀይለኛ እጆች\" የሚለው የሚያመለክተው የእርሱን በኤርምያስ ላይ ቁጥጥር ማድረግ እና ተጽዕኖ ማሳረፍ ነው፡፡ \"አንተ በሀይል ተጫንከኝ\" ወይም \"በማደርገው ላይ ተጽዕኖ/ቁጥጥር ያደረግከው አንተ ነህ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስቃዬ ስለምን በዛ፣ ቁስሌስ ለምን የማይድን ሆነ?",
"body": "ኤርምያስ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ስቃዩን አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ ስለ ስቃዩ የሚናገረው አካላዊ ቁስል እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር መለክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ \"ስቃዬ ቀጥሏል፣ እንደማይድን ቁስል ነው\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ለመፈወስ አልወደደም",
"body": "ይህ የኤርምያስ ቁስል መፈወስ እንዳልወደደ ሰው ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ ይህ አድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ \"የማይፈወስ\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ ለእኔ እንደሚያታልል እና እንደሚደርቅ ውሃ ትሆንብኛለህን?",
"body": "ኤርምያስ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው በያህዌ ላይ መደገፍ እንደማይችል ሆኖ የተሰማውን ስሜት ለማጉላት ነው፡፡ ይህንን የተናገረው ያህዌ እንደሚደርቅ ወራጅ እንደሆነበት አጉልቶ ለመናገር ነው፡፡ \"አንተ ለእኔ ሊታመኑበት እንደማይችለሁት፣ ውሃ ልቀዳ ሄጄ ደርቆ እንዳገኘሁት ወራጅ እንደሆንክብኝ ያሀል ተሰምቶኛል፡፡\" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)"
}
]