am_jer_tn/14/17.txt

30 lines
2.2 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ቀንና ሌሊት",
"body": "እዚህ ላይ ሁልጊዜ ለማለት የቀኑ ሁለት ተቃራኒ ጊዜያቶች ተሰጥተዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሁልጊዜ፣ ቀንና ሌሊት በሙሉ” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሕዝቤ ድንግል ሴት ልጅ",
"body": "እዚህ ላይ እግዚብሔር የእርሱ ሕዝብ ለእርሱ ብርቅየና የተወደደ እንደሆነ ሲናገር እነርሱ የእርሱ ድንግል ሴት ልጅ እንደሆኑ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ድንግል ሴት ልጅ የምሳሳላቸው ሕዝቤ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የማይፈወስ ቁስል",
"body": "ሊፈወስ የማይችል በቆዳ ላይ የሚከሰት መቆረጥ ወይም ስብራት"
},
{
"title": "በሰይፍ የሞቱ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ በተጨማሪ “ሰይፍ” እዚህ ላይ ጦርነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሰይፍ የሞቱ ሰዎች” ወይም “በጦርነት የሞቱ ሰዎች” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በረሃብ ምክንያት የመጡ በሽታዎች አሉ",
"body": "እዚህ ላይ “በሽታዎች” የሚለው በረሃብ ከመሰቃየታቸው የተነሳ እነዚህ በሽታዎች ያሉባቸውን ሰዎች ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከረሃብ የተነሳ የታመሙ ሰዎች አሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይቅበዘበዛሉ",
"body": "ያለ ዓላማ ወዲህና ወዲያ መንቀሳቀስ"
},
{
"title": "አያውቁም",
"body": "እነርሱ ምን እንደማያውቁ መግለጹ ሊጠቅም ሊሆን ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምን እንደሚሰሩ አያውቁም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]