am_jer_tn/14/15.txt

26 lines
2.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስ ሐሰተኛ ነቢያቶች ስለሚተነብዩት ነገሮች ለእግዚአብሔር እየተናገረ ነበር፡፡ "
},
{
"title": "በስሜ",
"body": "ይህ ሀረግ በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን ወይም እንደ እርሱ ወኪል መናገርን ያመለክታል፡፡ ይህን በኤርምያስ 14:14 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ምንም ሰይፍ አይኖርም … ሰይፍ አይኖርም ",
"body": "እዚህ ላይ “ሰይፍ” ጦርነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምንም ጦርነት አይኖርም … ጦርነት አይኖርም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በዚያን ጊዜ ትንቢት የተነገረላቸውም ሕዝብ ከራብና ከሰይፍ የተነሣ በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ይበተናሉ ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይህ ማለት የቤተሰብ አባላት በሙሉ ይሞታሉ፣ ሕዝቡም አስከሬኖቻቸውን ከመቅበር ይልቅ በመንገዶቹ ላይ ይጥላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በዚያን ጊዜ ትንቢት የተነገረላቸው ሕዝብ በራብና በሰይፍ ይሞታሉ፣ ሕዝቡም አስከሬኖቻቸውን በኢየሩሳሌም መንገዶች ላይ ይጥሉአቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሚስቶቻቸውን፣ ወንዶች ልጆቻቸውን ወይም ሴቶች ልጆቻቸውን",
"body": "ይህ የሚያብራራው “እነርሱ” በሚለው ቃል የተመለከቱትን ሰዎች ነው፣ ይህም በራብና በሰይፍ የሞቱትን ሰዎች በሙሉ ማለት ነው፡፡"
},
{
"title": "እኔ ክፋታቸውን በእነርሱ ላይ አፈስስባቸዋለሁ",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር ሕዝቡን እንደ ክፋታቸው መጠን እንደሚቀጣቸው ሲናገር የሕዝቡ ክፋት ፈሳሽ እንደሆነና እርሱ ይህን ፈሳሽ በእነርሱ ላይ እንደሚያፈስስባቸው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ሊቀጡ እንደሚገባቸው እኔ እቀጣቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]