am_jer_tn/14/13.txt

30 lines
2.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ለኤርምያስ ለይሁዳ ሕዝብ እንዳይጸልይላቸው ነገረው፡፡"
},
{
"title": "ሰይፍ አታዩም",
"body": "እዚህ ላይ “ሰይፍ” ጦርነትን ይወክላል፣ “ማየት” ደግሞ በሁኔታው ውስጥ ማለፍን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በአንድም ጦርነት ውስጥ አታልፉም” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እውነተኛ ደህንነት እሰጣችኋለሁ",
"body": "እዚህ ላይ “ደህንነት” አንድ ሰው ለሌላ ሰው ሊሰጠው የሚችለው እቃ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ በደህንነት እድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ” ወይም “እኔ በሰላም እንድትኖሩ እፈቅድላችኋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የውሸት ትንቢት ይናገራሉ",
"body": "“ውሸት” የሚለው ቃል እንደ ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በመዋሸት ይተነብያሉ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በስሜ",
"body": "ይህ ሀረግ በእግዚአብሔር ኃይልና ስልጣን ወይም እንደ እርሱ ወኪል መናገርን ያመለክታል፡፡ (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ እነርሱን አልላክኋቸውም",
"body": "ይህ እግዚአብሔር ለሕዝቡ እንዲያስተላልፉ መልእክት ሰጥቶ አልላካቸውም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ ለሌሎች ሰዎች ትንቢት እንዲናገሩ አልላክኋቸውም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከራሳቸው አእምሮ የሚወጣ ",
"body": "እዚህ ላይ “አእምሮ” ሃሳብን የማሰብ ችሎታ ሳይሆን የሆነ ስፍራ እንደሆነ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ ራሳቸው ያሰቡትን” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]