am_jer_tn/14/07.txt

42 lines
3.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ በኩል ለሕዝቡ ስለ ድርቅ ተናግሯቸዋል፡፡"
},
{
"title": "ኃጢአታችን በእኛ ላይ ይመሰክርብናል",
"body": "እዚህ ላይ “ኃጢአቶች” ስለ ክፉ ስራቸው በእነርሱ ላይ የሚመሰክሩ ሰዎች እንደሆኑ ተደርጎ ተነግሯል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ኃጠአታችን ለክፉ ስራችን ማስረጃ ይሰጣሉ” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለ ስምህ ብለህ",
"body": "እዚህ ላይ የእግዚአብሔር “ስም” መልካም ማንነቱን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስለ መልካም ማንነትህ ብለህ” ወይም “ማንኛውም ሰው አንተ በጣም ታላቅና ቃል ኪዳንህን የምትጠብቅ እንደሆንህ ማየት ይችል ዘንድ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ተስፋ",
"body": "ይህ የእግዚአብሔር ሌላ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ የእስራኤል ተስፋ ነህ” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ በምድር እንደ እንግዳ ለምን ትሆናለህ … ግራ እንደተጋባ ሰው ለምን ትሆናለህ ",
"body": "እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ሁለቱም ጥያቄዎች እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ግድ የማይሰኝ እንደሆነና እነርሱን ለመርዳት የማይችል እንደሆነ ይጠይቃሉ፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንተ በምድር እንደ እንግዳ ለምን ትሆናለህ፣ እንደ ባዕድ መንገደኛ … አንድ ሌሊት ብቻ",
"body": "ይህ ጥያቄ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመርዳት ቸልተኛ የሆነበት ሁኔታ እንዳለ ሲናገር እርሱ በዚያ ስፍራ ስለሚኖሩ ሰዎች ግድ የሌለው በዚያ መንገድ የሚያልፍ እንግዳ መንገደኛ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በዚያ የሚያልፍና አንድ ሌሊት ብቻ የሚያድር ሰው",
"body": "ሁለቱም ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ስለዚህ በአንድ ላይ ሊጣመሩ ይችላሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለአንድ ሌሊት ብቻ የሚቆይ” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ግራ እንደተጋባ ሰው፣ ወይም ያድን ዘንድ እንደማይችል ተዋጊ ስለ ምን ትሆናለህ? ",
"body": "ይህ እግዚአብሔር ሕዝቡን ለመርዳት ያልቻለበት ሁኔታ እንዳለ ሲናገር እርሱ ማንንም ሰው ማዳን ያልቻለ ግራ የተጋባ ተዋጊ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጾአል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ግራ መጋባት",
"body": "አንድን ነገር ለመረዳት ወይም በግልጽ ለማሰብ አለመቻል"
},
{
"title": "ስምህ በእኛ ላይ ተጠርቷል",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ ይህ ስሙ በእነርሱ ላይ እንደተጠራ በመናገር ሕዝቡ የእግዚአብሔር ሕዝብ እንደሆኑ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ስምህን ተሸክመናል” ወይም “እኛ የአንተ ሕዝብ ነን” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ and ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]