am_jer_tn/14/04.txt

26 lines
2.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር በነቢዩ በኤርምያስ በኩል ስለ ድርቅ ለሕዝቡ መናገሩን ቀጥሏል፡፡"
},
{
"title": "አራሾች አፈሩ ራሳቸውንም ተከናነቡ",
"body": "በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ሰዎች እፍረታቸውን ለማሳየት ራሳቸውን የሚሸፍኑበት ልብስ ይለብሱ ነበር፡፡ (ምሳሌያዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሜዳ አጋዘን ግልገሎቿን በሜዳ ተወች፣ ግልገሎቿን ተወቻቸው",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የሚበላ ነገር ባለመኖሩና ልትሰጣቸው ስላልቻለች የሜዳ አጋዘን ግልገሎቿን በሜዳ እንደ ተወች አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሜዳ አጋዘን ግልገሎቿን በሜዳ ተወች” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሳር የለምና",
"body": "ለአጋዘን የሚሆን የሚበላ ሳር የለም ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእነርሱ የሚሆን የሚበላ ሳር የለምና” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደ ቀበሮም በነፋስ ውስጥ አለከለኩ",
"body": "ይህ እንደ ቀበሮ አለከለኩ በማለት አህዮች ማለክለካቸው ይናገራል ምክንያቱ ደግሞ ጥም ስለበረታባቸው ነው፡፡ ቀበሮ ብዙ የሚያለከልኩ በጣም አደገኛ የሆኑ የዱር ውሻዎች ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንደ ተጠማ ቀበሮ በነፋስ ውስጥ ያለከልካሉ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አትክልት የለምና ዓይኖቻቸው ፈዘዙ",
"body": "“የሚበሉት ሳር ስለሌለ ታወሩ”"
}
]