am_jer_tn/13/18.txt

26 lines
2.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ለኤርምያስ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ እርሱ ለይሁዳ ንጉስና ለንጉሱ እናት ምን እንደሚላቸው ለኤርምያስ እየነገረው ነው፡፡"
},
{
"title": "ንግስት እናት",
"body": "የንጉስ እናት"
},
{
"title": "የክብራችሁ አክሊል ከራሳችሁ ወርዶአልና ",
"body": "ንጉሱና ንግስቲቱ እናት እንደ ንጉስና እንደ ንግስት እናት ንጉሳዊ ስልጣናቸውን እንዲወክል አክሊል በራሳቸው ላይ ያደርጋሉ፡፡ በተጨማሪ ይህ ክስተት ገና አልተፈጸመም ነገር ግን እዚህ ላይ ግን ክስተቱ እንደከናወነ ተደርጎ ተጽፏል፡፡ ይህ በወደፊት ጊዜ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእንግዲህ ወዲህ ንጉስና ንግስት እናት አትሆኑም፤ አክሊሎቻችሁ፣ ኩራታችሁና ክብራችሁ በሙሉ ይወድቃል” (ምሳሌያዊ ድርጊት እና የተፈጸመ ትንቢታዊ ንግግር የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፣ የሚከፍታቸውም አይኖርም",
"body": "ይህ ከተሞቹ ማንም ሰው ወደ ውስጥ እንዳይገባ ወይም ከከተሞቹ እንዳይወጣ ለመከልከል በጠላቶቻቸው ይከበባሉ ማለት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ፣ አንድም ሰው ወደ ከተሞቹ መግባት ወይም ከእነርሱ መውጣት አይችልም” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በኔጌቭ ያሉ ከተሞች ይዘጋሉ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቻችሁ በላይ በኔጌቭ ያሉትን ከተሞች ይዘጓቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይሁዳ በሙሉ ይማረካል፣ ሙሉ በሙሉ ምርኮኛ ሆኖ ይወሰዳል",
"body": "እዚህ ላይ “ይሁዳ” በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ይወክላል፡፡ ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶች የይሁዳን ሕዝብ በሙሉ ምርኮኛ አድርገው ወደ ግዞት ይወስዷቸዋል” (ምትክ ስም እና ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]