am_jer_tn/13/12.txt

38 lines
3.5 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል … ማድጋ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ማንኛውም የወይን አቁማዳ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል … ማንኛውም የወይን አቁማዳ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል” ወይም “ማንኛውም የወይን ማሰሮ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል … ማንኛውም የወይን ማሰሮ ሁሉ በወይን ጠጅ ይሞላል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ተመልከቱ",
"body": "ይህ ቃል እዚህ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ቀጥሎ የሚናገረውን ንግግር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዳምጡ” ወይም “ለምነግራችሁ ነገር ትኩረት ስጡ”"
},
{
"title": "በዚህች ምድር የሚኖሩትን ሁሉ በስካር እሞላቸዋለሁ",
"body": "“የዚህችን ምድር ነዋሪዎች በሙሉ እንዲሰክሩ አደርጋቸዋለሁ”"
},
{
"title": "በዳዊት ዙፋን የሚቀመጡትን ነገሥታት",
"body": "እዚህ ላይ የይሁዳ ንጉስ የሚቀመጥበት ዙፋን “የዳዊት ዙፋን” በሚለው ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በይሁዳ ዙፋን የሚቀመጡ ነገስታት” ወይም “የይሁዳ መንግስት ነገስታት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እያንዳንዱን ሰው ከሌላው ሰው ጋር፥ አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ፥ እቀጠቅጣለሁ",
"body": "እዚህ ላይ “እያንዳንዱ ሰው” የሚሉት ቃላቶች ወንዶችንና ሴቶችን በሙሉ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከዚያም እኔ ሕዝቡ እርስ በርሳቸው እንዲጣሉ አደርጋቸዋለሁ፣ ወላጆችና ልጆች ሳይቀር እርስ በርሳቸው ይጣላሉ” (የተባዕት ቃላት ሴቶችንም ሲያካትት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አባቶችና ልጆች በአንድ ላይ ",
"body": "ግልጽ የሆነው መረጃ ሊቀርብ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አባቶችንና ልጆችን በአንድ ላይ እቀጠቅጣቸዋለሁ” (አስጨምሬ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "አላዝንላቸውም",
"body": "“ሃዘን ፈጽሞ አይሰማኝም”"
},
{
"title": "ከጥፋት አላድናቸውም",
"body": "“ቅጣቱን ከእነርሱ አልመልስም፡፡” ይህ በአዎንታዊ መልኩ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንዲጠፉ እፈቅዳለሁ” "
}
]