am_jer_tn/13/08.txt

38 lines
3.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "የእግዚአብሔር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ",
"body": "“የእግዚአብሔር ቃል መጣ” የሚለው ፈሊጥ ሲሆን ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣውን ልዩ መልእክት ለማስተዋወቅ የሚጠቅም ነው፡፡ ይህንን በኤርምያስ 1:4 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከትና እንደ አስፈላጊነቱ ማንኛውንም ለውጥ አድርግ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር ለሁለተኛ ጊዜ መልእክት ሰጠኝ፡፡ እንዲህም አለኝ፡-“ ወይም “እግዚአብሔር ይህን ሁለተኛውን መልእክት ለእኔ ተናገረኝ፡-“ (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የይሁዳና የእስራኤል",
"body": "እዚህ ላይ የይሁዳና የኢየሩሳሌም የሚለው የሚያመለክተው በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የይሁዳና የኢየሩሳሌም ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቃሌን ለመስማት",
"body": "“እኔ የተናገርሁትን ለመታዘዝ”"
},
{
"title": "በልባቸውም እልከኝነት የሚሄዱ",
"body": "ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጣም እልከኞች የሆኑና ምኞታቸውን ብቻ የሚያደርጉ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንደምትጣበቅ … ከእኔ ጋር አጣብቄአለሁ",
"body": "“እንደሚለጠፍ … ከእኔ ጋር ተለጥፈዋል” ወይም “ተጠግተው እንደሚቆዩ … ከእኔ ጋር ተጠግተው ቆይተዋል”"
},
{
"title": "ቤት ሁሉ … ቤት ሁሉ",
"body": "“ሕዝብ ሁሉ … ሕዝብ ሁሉ”"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት",
"body": "“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ እዚህ ላይ የእስራኤልን መንግስት ያመለክታል፡፡ ይህን በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እስራኤል” ወይም “የእስራኤል መንግስት” ወይም “የእስራኤል ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "የይሁዳ ቤት",
"body": "“ቤት” የሚለው ቃል በቤት ውስጥ ለሚኖሩት ቤተሰቦች ምትክ ስም ነው፡፡ እዚህ ላይ የይሁዳንና የቢንያምን ልጆች የሚያካትተውን የይሁዳን መንግስት ያመለክታል፡፡ ይህን በኤርምያስ 3፡18 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ይሁዳ” ወይም “የይሁዳ መንግስት” ወይም “የይሁዳ ሕዝብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]