am_jer_tn/12/10.txt

26 lines
1.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተውታል",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር ምድሩና ሕዝቡ በጠላቶች ስለ መጥፋታቸው ሲናገር ሕዝቡ እረኛው እንዳጠፋው እንደ ወይን ቦታ አድርጎ ገልጦአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሕዝቤና ምድሬ ብዙ እረኞች እንዳጠፉት የወይን ቦታ ናቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ብዙ እረኞች አጥፍተውታል",
"body": "እዚህ ላይ “እረኞች” የሚለው ቃል በጎቻቸውን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ብዙ እረኞች በጎቻቸው እንዲያጠፉት ፈቅደውላቸዋል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሁሉንም ረጋግጠውታል",
"body": "“በእግራቸው ረጋግጠውታል”"
},
{
"title": "እድል ፈንታዬ የሆነው ምድር",
"body": "“እኔ የተከልሁት ቦታ” ወይም “የእኔ እርሻ”"
},
{
"title": "ምድሪቱ ባድማ ሆናለች",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሪቱ በሙሉ ባድማ ሆናለች” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በልቡ የሚያስባት",
"body": "ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሚንከባከባት” ወይም “ትኩረት የሚሰጣት” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]