am_jer_tn/12/07.txt

46 lines
5.1 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ። የምትወድዳትን በጠላቶችዋ እጆች አሳልፌ ሰጥቻለሁ።",
"body": "እነዚህ ሶስት ዓረፍተ ነገሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ አንደኛውና ሁለተኛው ዓረፍተ ነገሮች የሶስተኛውን ሃሳብ ያጠናክራሉ፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቤቴን ትቼአለሁ፣ ርስቴንም ጥያለሁ",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር “ቤቱ” እና “ርስቱ” እንደሆኑ አድርጎ የገለጸበት ተለዋጭ ዘይቤ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ለእኔ እንዲሆኑ የመረጥኋቸውን የእኔ የሆኑትን የእስራኤልን ሕዝብ ትቻቸዋለሁ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በጠላቶችዋ እጆች",
"body": "እዚህ ላይ “እጆች” የሚለው በቁጥጥር ስር ማድረግን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጠላቶቿ ለመሸነፍ” ወይም “በጠላቶቿ ቁጥጥር ስር እንድትሆን” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእርሷ … እርሷ ተነሳችብኝ … ከእርሷ ጋር … እርሷን ጠላኋት",
"body": "እዚህ ላይ ሕዝቡን የአንስታይ ጾታ ተውላጠ ስም በመጠቀም እግዚአብሔር ሕዘቡን እንደ ሴት ይጠራዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱ … እነርሱ … ራሳቸውን አዘጋጁ … ከእነርሱ ጋር … እነርሱን ጠላኋቸው” (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሷ በራሷ ድምጽ በእኔ ላይ ተነሳችብኝ",
"body": "ይህ የእግዚአብሔርን ሕዝብ እንደ አንበሳ አድርጎ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ይህ ሕዝቡ በእግዚብሔር ላይ እንደሚያገሱ አድርጎ በመግለጽ እነርሱ በእግዚብሔር ላይ እንደተነሱ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔን ለመቃወም በእኔ ላይ እንደምታገሳ ሆናለች”"
},
{
"title": "የተወደደች ርስቴ ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን? ",
"body": "እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው ሕዝቡ በጠላቶቻቸው እንደተከበቡ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የተወደደች ርስቴ በዙርያዋ ሁሉ እንደተከበበች እንደ ዝንጉርጉር አሞራና ሌሎች የሚታደኑ ወፎች ሆናለች፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የተወደደች ርስቴ ",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር ስለ ሕዝቡ ሲናገር የእርሱ “የተወደዱ ርስት” እነደሆኑ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ሕዝብ፣ የተወደዱ ሕዝቤ … አይደሉምን” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሌሎች አሞሮች ሊበሏት እንደ ከበቧት እንደ ዝንጕርጕር አሞራ አልሆነችምን? ",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር በአደጋ ላይ ስላለውና በጠላቶቹ ስለተከበበው ስለ ሕዝቡ ሲናገር በአዳኝ ወፎች እንደተከበበ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሷ እንደ ዝንጉርጉር አሞራ ሆነች፣ ጠላቶቿም ደግሞ በሁሉም አቅጣጫ እርሷን እንደሚያጠቁ እንደ አዳኝ ወፎች ሆነዋል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዝንጕርጕር አሞራ ",
"body": "“ያልተለመደ መልክ ያለው እንግዳ ወፍ፡፡” ይህ ብዙ ጊዜ በሌሎች ወፎች የሚታደንና የሚበላ ወፍን ያመለክታል፡፡"
},
{
"title": "አደን የሚድኑ አሞሮች",
"body": "እንስሳትን የሚያጠቁና የሚበሉ ወፎች"
},
{
"title": "ሂዱ፥ የምድር አራዊትን ሁሉ ሰብስቡ፥ ይበሏትም ዘንድ አምጡአቸው",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር ለማጠናከር በትዕዛዝ መልክ ይናገራል፡፡ ይህ ትዕዛዝ የተሰጠው ለተወሰነ ግለሰብ አይደለም ስለዚህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በሜዳ ያሉ የምድር አራዊት ሁሉ ይምጡና ይብሏት” (እንቶኔ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]