am_jer_tn/12/03.txt

34 lines
2.4 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስ ለእግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል፡፡\t"
},
{
"title": "ልቤ",
"body": "እዚህ ላይ “ልብ” የሰውን ሃሳብና እውነተኛ ስሜት ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኔ ሃሳቦች” ወይም “የእኔ የውስጥ ስሜት” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ወደ ዕርድ ቦታ እንደሚወሰዱ በጎች ውሰዳቸው",
"body": "እዚህ ላይ ኤርምያስ ክፉ ሰዎችን ለመቅጣት እንዲዘጋጅ እግዚብሔርን ሲጠይቅ እነርሱ ለመታረድ እንደሚወሰዱ በጎች እንደሆኑ አድርጎ ገልጾአቸዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ክፉ ሰዎችን ለመታረድ እንደሚነዱ በጎች ውሰዳቸው” ወይም “ክፉ ሰዎችን ለመቅጣት ተዘጋጅ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የዕርድ ቀን",
"body": "“እነርሱ የሚጠፉበት ቀን”"
},
{
"title": "በእርሷ ከሚኖሩት ሰዎች ክፋት የተነሳ ምድሪቱ የምትደርቀው እስከ መቼ ነው? ",
"body": "በሰዎች ክፋት ምክንያት ቅጣት ስለተላለፈባቸው ምድራቸው ደርቃለች፣ ዝናብ ደግሞ አይዘንብም፡፡"
},
{
"title": "መጠውለግ",
"body": "መድረቅ"
},
{
"title": "እንስሳቱና ወፎቹ ተወስደዋል",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እንስሳቱና ወፎቹ ሄደዋል” ወይም “እንስሳቱና ወፎቹ በሙሉ ሞተዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እግዚአብሔር በእኛ ላይ የሚሆነውን ነገር አያይም",
"body": "ሊሆኑ የሚችሉ ትርጉሞች፡- 1) ሕዝቡ በወደፊት ሕይወታቸው በእነርሱ ላይ ምን ነገሮች እንደሚፈጸሙ እግዚአብሔር አያውቅም እያሉ ይናገራሉ ወይም 2) እግዚአብሔር ኃጢአታቸውን አያውቅም፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር እኛ የምንሰራቸውን ኃጢአት የተሞሉ ነገሮችን አያይም” "
}
]