am_jer_tn/11/21.txt

42 lines
2.9 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ዓናቶት",
"body": "ይህ ካህናት የሚኖሩበት የተለየ ከተማ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሕይወትህን ለሚፈልጓት",
"body": "ይህ ሀረግ የሚያመለክተው አንድን ሰው ለመግደል መፈለግ ወይም መሞከር ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተን ለመግደል መፈለግ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እንዲህ አሉ",
"body": "“ለእኔ እንዲህ አሉኝ፡፡” ሰዎቹ ለኤርምያስ እየተናገሩ ነው፡፡ "
},
{
"title": "በእጃችን ትሞታለህ",
"body": "እዚህ ላይ ሰዎቹ “እጃችን” የሚለውን ቃል የተጠቀሙት እነርሱ ራሳቸው እርሱን ለመግደል ማቀዳቸውን አጽንዐት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ ራሳችን እንገድልሃለን” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል",
"body": "ኤርምያስ ከእግዚአብሔር የመጣውን በጣም አስፈላጊ መልእክት ለማስተዋወቅ ብዙ ጊዜ እነዚህን ቃላት ይጠቀማል፡፡ ይህን በኤርምያስ 6፡6 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡"
},
{
"title": "ተመልከቱ",
"body": "ይህ ቃል እዚህ ላይ ጥቅም ላይ የዋለው ቀጥሎ የሚናገረውን ንግግር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አዳምጡ” "
},
{
"title": "ኃይለኛ ወጣት ወንዶች",
"body": "እነዚህ በጣም ጠንካራ በሚሆኑበት የሕይወት እድሜ የሚገኙ ናቸው"
},
{
"title": "በሰይፍ ይሞታሉ",
"body": "እዚህ ላይ “ሰይፍ” ጦርነትን ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በጦርነት ውስጥ ይሞታሉ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "አንዳቸውም አይተርፉም",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ አንዳቸውንም አልተዋቸውም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በሚቀጡበት ዓመት",
"body": "እዚህ ላይ “ዓመት” የሚለው ቃል ፈሊጥ ሲሆን እግዚአብሔር የወሰነውን የተለየ ጊዜ የሚገልጽ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነርሱ በሚቀጡበት ጊዜ” ወይም “እነርሱ የሚቀጡበት ጊዜ እየመጣ ነው” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]