am_jer_tn/11/18.txt

38 lines
3.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች እንዳውቃቸው አደረገኝ፣ እኔም አወቅኋቸው",
"body": "“አንተ ነገሮችን ለእኔ ገለጥህልኝ፣ እኔም አወቅኋቸው፡፡” ይህ ጠላቶቹ እርሱን ለመግደል እያቀዱ እንደነበረ እግዚአብሔር ለኤርምያስ መግለጡን የሚያመለክት ነው፡፡"
},
{
"title": "ስራቸውን እንድመለከት አደረግኸኝ",
"body": "ይህ ጠላቶቹ እርሱን ለመግደል እያቀዱ እንደነበረ እግዚአብሔር ለኤርምያስ መግለጡን የሚያመለክት ነው፡፡ እዚህ ላይ የተነገረው ኤርምያስ የእነርሱን ስራዎች እንደተመለከተ አድርጎ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነርሱን ክፉ እቅዶች ለእኔ ገለጠልኝ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔም ለመታረድ እንደሚነዳ እንደ የዋህ በግ ጠቦት ሆንሁ",
"body": "ይህ ኤርምያስን ለመታረድ ከሚነዳ ከየዋህ በግ ጋር በማነጻጸር ኤርምያስ እርሱን ለመግደል ጠላቶቹ ያቀዱትን እቅድ አለማወቁን ይናገራል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ለመታረድ ወደ እርድ ቦታ እንደሚነዳ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቶቼ ወደ እርድ ቦታ እየመሩኝ ነው” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ዛፉን ከፍሬው ጋር እንቍረጥ",
"body": "እዚህ ላይ የኤርምያስ ጠላቶች እርሱን ለመግደል ስለማሰባቸው ሲናገር ኤርምያስ እነርሱ ሊያጠፉት ያቀዱት የፍሬ ዛፍ እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እርሱን ከሕያዋን ምድር እናጥፋው",
"body": "“እናጥፋው” የሚለው ቃል እርሱን ማጥፋት ማለት ነው፡፡ በተጨማሪ “ሕያዋን” የሚለው ሕያዋን ሕዝብን ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “በእነዚህ በሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ምድር ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይኖር እንግደለው” ወይም “በሕይወት በሚኖሩ ሰዎች ዓለም መካከል ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይኖር እናጥፋው” ( ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስሙም ከእንግዲህ ወዲህ እንዳይታሰብ ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰዎች ከእንግዲህ ወዲህ ስሙን አያስታውሱትም” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልብንና አእምሮን",
"body": "“ልብ” የሚለው ሰው ለሚሰማው ስሜትና ለሚፈልገው ነገር ምትክ ስም ነው፣ “አእምሮ” ደግሞ ሰው ለሚያስበውና ለሚወስነው ነገር ምትክ ስም ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰው ስሜትና ሃሳብ” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በቀልህን እኔ እመሰክራለሁ",
"body": "እዚህ ላይ “በቀል” የሚለው ቃል በግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አንተ ስትበቀል እኔ እመለከትሃለሁ” (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ) "
}
]