am_jer_tn/11/14.txt

30 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "ስለ እነርሱ ልትማጠን አይገባህም",
"body": "“ታላቅ የሃዘን ልቅሶ ልታለቅስ አይገባህም”"
},
{
"title": "ወዳጄ፣ እጅግ በጣም ብዙ ክፉ ሃሳብ የነበራት በቤቴ ውስጥ ምን አላት?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመበት የይሁዳ ሕዝብ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ለወደፊት ለመገኘት ምንም ዓይነት መብት እንደሌለው አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- ወዳጄ፣ እጅግ በጣም ብዙ የክፋት ሃሳብ የነበራት፣ በቤቴ ውስጥ ልትገኝ አይገባትም፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህች ወዳጄ፣ የነበራት",
"body": "የይሁዳ ሕዝብ እጅግ እንደተወደደች እንደ አንዲት ሴት ተደርጋ ተነግራለች፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የምወዳቸው ሕዝቤ፣ የነበራቸው” ወይም “እኔ የምወዳቸው የይሁዳ ሕዝብ፣ የነበራቸው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ባለፉት ዘመናት እግዚአብሔር የለመለመ የወይራ ዛፍ ብሎ ጠርቶሽ ነበር",
"body": "በብሉይ ኪዳን ሰዎች ብዙ ጊዜ ከዛፎችና ከተክሎች ጋር ይነጻጸሩ ነበር፡፡ ፍሬያማና ጤናማ የነበሩት የለመለሙና ጤናማ ዛፎች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ባለፉት ዘመናት እግዚአብሔር እናተ እንደለመለመ የወይራ ዛፍ እንደነበራችሁ ተናግሯል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በእርሷ ላይ እሳት ያነድድባታል",
"body": "ይህ ገለጻ የዛፉን ተለዋጭ ዘይቤ ተከትሎ የተነገረ ነው፡፡ እሳቱ የሚወክለው የሕዝቡን መጥፋት ነው፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህም የታላቅ ዓውሎ ነፋስ ድምጽ ይኖረዋል",
"body": "ይህ የአስከፊውን እሳት ድምጽ ከኃይለኛ ዓውሎ ነፋስ ድምጽ ጋር ያኘጻጽረዋል፡፡ (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቅርንጫፎቹ ይሰባበራሉ",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ቅርንጫፎችሽን ይሰባብራቸዋል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]