am_jer_tn/10/19.txt

34 lines
3.6 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "ኤርምያስ እርሱ መላው የእስራኤል ነገድ እንደሆነ አድርጎ ይናራል፡፡ (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እኔ ወዮልኝ! በተሰበሩ አጥንቶቼ ምክንያት፣ ቁስሌ የማይድን ነው",
"body": "ኤርምያስ ስለ ሕዝቡ ጉዳት ሲናገር በተሰበሩ አጥንቶችና በማይድን ቁስል በአካል እንደተጎዱ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኛ ወዮልን! የተሰበረ አጥንትና የማይድን ቁስል እንዳለን ያህል ነው” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነገር ግን ልሸከመው ይገባኛል",
"body": "እዚህ ላይ ኤርምያስ የእስራኤልን መላውን ነገድ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ነገር ግን ልንሸከመው ይገባናል” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድንኳኔ ፈርሷል፣ የድንኳኔ ገመዶች ሁሉ ለሁለት ተቆርጠዋል",
"body": "እዚህ ላይ ኤርምያስ ጠላት ከተማቸውን ስለማፍረሱ ሲናገር ድንኳኑ እንደፈረሰ አድርጎ ተናግሮታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኛ ታላቅ ድንኳን የፈረሰ ያህል ነው፤ ድንኳኑን የሚያያይዙት ገመዶች ተቆርጠዋል” ወይም “ጠላት ከተማችንን ሙሉ በሙሉ አፍርሷታል” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድንኳኔ ፈርሷል",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊገለጽ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጠላቴ ድንኳኔን አፍርሶታል” ወይም “የእኛ ጠላት ድንኳናችንን አፍርሶታል” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ልጆቼን ከእኔ አርቀው ወስደዋቸዋል",
"body": "እዚህ ላይ ኤርምያስ የእስራኤልን መላውን ነገድ ይወክላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእኛ ጠላቶች ልጆቻችንን ከእኛ አርቀው ወሰደዋቸዋል” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ስለዚህ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖሩም",
"body": "ልጆቹ ከእንግዲህ ወዲህ አይኖሩም የሚለው ወላጆች ከእንግዲህ ወዲህ እንደገና ሊያዩአቸው እንደማይችሉ ለመግለጥ ተለዋጭ ዘይቤ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከእንግዲህ ወዲህ እንደማይኖሩ ዓይነት ነው” ወይም “እነርሱ እንደገና ፈጽሞ አይመለሱም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከእንግዲህ ወዲህ ድንኳኔን የሚዘረጋ ወይም የድንኳኔን መጋረጃዎች የሚያነሣ ማንም የለም",
"body": "እዚህ ላይ ኤርምያስ ከተማቸውን እንደገና ለመገንባት አንድም ልጅ እንደማይኖርላቸው ስለ እነርሱ ሲናገር ከተማቸው እንደገና ልትገነባ የሚገባት ድንኳን እንደነበረች አድርጎ ገልጾታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከተማችንን እንደገና ለመገንባት አንድም ሰው አይኖርም” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]