am_jer_tn/10/11.txt

34 lines
2.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ለኤርምያስ እየተናገረው ነው፡፡"
},
{
"title": "እናንተም ለእነርሱ እንዲህ ብላችሁ ትነግሩአቸዋላችሁ",
"body": "“እናንተ” የሚለው ቃል እስራኤላውያንን ይወክላል፣ “እነርሱን” የሚለው ደግሞ የሌሎች መንግስታት ሕዝቦችን ይወክላል፡፡"
},
{
"title": "ከምድር ይጠፋሉ",
"body": "ይህ ጣዖቶቹ እንደሞቱ ተቆጥረው ስለ መጥፋታቸውና ጠቃሚነታቸውን ስለ ማጣታቸው ይናገራል፡፡ ይህ እነርሱ ኃይል እንደሌላቸው አጽንዖት ይሰጣል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ከምድር ይጠፋሉ” ( ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰማያትንም የዘረጋ",
"body": "ይህ እርሱ እንደዘረጋው እንደ ትልቅ አንሶላ እግዚአብሔር ሰማያትን እንደፈጠረ ይናገራል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰማጣትን ፈጠረ” ወይም “ሰማይን ፈጠረ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ድምጹ በሰማያት ያሉ ውሆች እንዲናወጡ ያደርጋል",
"body": "እዚህ ላይ ለንግግሩ አጽንዖት ለመስጠት እግዚአብሔር “በድምጹ” ተወክሏል፡፡ “ውሆች” እንዲናወጡ የሚለው ሀረግ ታላቅ ጩኸት ያለውን ማዕበል ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእርሱ ድምጽ በሰማይ ማዕበል ይፈጥራል” (ምትክ ስም የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ጉምን ከምድርም ዳር ወደ ላይ እንዲወጣ ያደርገዋል",
"body": "ይህ እርሱ ጉም ወደ ላይ እንዲተንንና ደመና እንዲፈጠር ያደረርጋል ማለት ነው፡፡ “ከምድርም ዳር” የሚለው ሀረግ ምድርን ሁሉ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እርሱ በማንኛውም የምድሪቱ ክፍል ሁሉ ደመና እንዲፈጠር ያደርጋል” (ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ነፋስንም ከግምጃ ቤቱ ይልካል",
"body": "ይህ እግዚአብሔር ነፋሳትን እንዲነፍሱ ስለማድረጉ ሲናገር ነፋሱ በግምጃ ቤት እንደተቀመጠና እርሱ ሲፈልግ እንደሚወጣ ተደጎ ተገልጦአል፡፡ (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ግምጃ ቤት",
"body": "የተለያዩ ቁሳቁሶች የሚቀመጡበት ሕንጻ"
}
]