am_jer_tn/09/25.txt

34 lines
3.7 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እነዚህ የእግዚአብሔር ቃላት ናቸው፡፡"
},
{
"title": "ተመልከቱ",
"body": "እግዚአብሔር እዚህ ላይ ይህን ቃል የተጠቀመው ከዚህ ክፍል ቀጥሎ የሚናገረውን ንግግር ሰዎች ትኩረት እንዲሰጡት ለማድረግ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “አድምጡ” ወይም “በእርግጥ” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቀናት እየመጡ ነው",
"body": "ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ጊዜ ይኖራል” (ፈሊጥ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "ስጋቸውን ብቻ የተገረዙትን",
"body": "ይህ በስጋቸው በመገረዝ ወደ እግዚአብሔር ቃል ኪዳን የገቡትን ነገር ግን የእርሱን ሕግ በመከተል ውስጣዊ ማንነታቸውን ያልለወጡ የእስራኤልን ሕዝብ የሚያመለክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ውጫዊ ሰውነታቸውን በመገረዝ የለወጡ ነገር ግን ውስጣዊ ማንነታቸውን ያልለወጡ ሕዝብ በሙሉ” (ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "በራሳቸው ላይ ያለውን ጸጉር በአጭሩ የሚቆረጡ ሕዝቦች በሙሉ",
"body": "ይህ ምናልባት የሚያመለክተው የአሕዛብ ጣዖት ለማክበር ሲሉ ጸጉራቸውን በአጭሩ የሚቆረጡ ሕዝቦችን ነው፡፡ አንዳንድ አዳዲስ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህን የዕብራይስጥ አገላለጽ “በምድረ በዳ ጫፍ ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች በሙሉ” ብለው ተርጉመውታል፡፡"
},
{
"title": "እነዚህ ሕዝቦች የተገረዙ አይደሉምና",
"body": "እዚህ ላይ “ሕዝቦች” የሚለው ቃል በእነዚህ ስፍራዎች የሚኖሩትን ሕዝቦች ነው፡፡ ያልተገረዙ እንግዳ ሰዎች በእግዚአብሔር ኪዳን ውስጥ ያልተካተቱ ለመሆናቸው ምልክት ነው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእነዚህ መንግስታት ሕዝቦች በመገረዝ ወደ እግዚአብሔር ኪዳን አልገቡም” (ምትክ ስም እና ግምታዊ እውቀት እና ያልተገለጸ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእስራኤል ቤት በሙሉ ያልተገረዘ ልብ አላቸው",
"body": "“ልብ” የሰውን ፈቃድና ፍላጎት ይወክላል፡፡ “ያልተገረዘ ልብ” እግዚአብሔርንና ሕጉን የማይከተል ሰው ባህርይ ይወክላል፡፡ ከዚህ በተጨማሩ የእስራኤል “ቤት” የእስራኤልን ሕዝብ ያመለክታል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእስራኤልን ሕዝብ በሙሉ የተገረዙት በውጫዊው ሰውነታቸው ብቻ ነው፣ ልባቸው ግን አልተለወጠም” (ምትክ ስም እና ተለዋጭ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]