am_jer_tn/09/21.txt

38 lines
3.3 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እዚህ ላይ እግዚአብሔር የሚናገረው እርሱ ምድሪቱን ሲያጠፋ ወደፊት የይሁዳ ሕዝብ የሚናገረውን ነው፡፡ "
},
{
"title": "ወጣት ወንዶች … በከተማይቱ አደባባይ … ሞት በመስኮታችን በኩል መጥቶአል ",
"body": "የይሁዳ ሕዝብ ለወደፊት ሞትን በመስኮት ዘልሎ በመግባት በቤት ውስጥ ያሉትን ሰዎች ለማጥቃትና በቤተ መንግሰት፣ በመንገዶችና በከተማ አደባባዮች ያሉትን ሰዎች ከሚያጠቃ ሰው ጋር ያነጻጽሩታል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ቤተ መንግስታት",
"body": "ነገስታት የሚኖሩበት በጣም የሚያምሩ ቤቶች፡፡ ሞት በተመሳሳይ መልኩ ወደ ባለጠጎችና ድሆች ይመጣል፡፡"
},
{
"title": "የከተማይቱ አደባባይ ",
"body": "የገበያ ስፍራዎች"
},
{
"title": "ይህ የእግዚአብሔር አዋጅ ነው",
"body": "እግዚአብሔር የሚናገረው ነገር እርግጠኛ እንደሆነ ለመግለጽ በስም ስለ ራሱ ይናገራል፡፡ ይህን በኤርምያስ 1፡8 ላይ እንዴት እንደተረጎምኸው ተመልከት፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር የተናገረው ይህ ነው” ወይም “እኔ እግዚአብሔር የተናገርሁት ይህ ነው” (አንደኛ፣ ሁለተኛና ሶስተኛ መደብ የሚለውን ይመልከቱ) "
},
{
"title": "የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ … ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ይወድቃል",
"body": "እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ የሰው ሬሳ እጅግ በጣም ብዙ መሆኑን አጽንዖት ይሰጣሉ፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የሰዎች ሬሳ በየቦታው ይወድቃል” (ትይዩነት/ተመሳሳይነት የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የሰውም ሬሳ እንደ ጕድፍ በእርሻ ላይ ይወድቃል",
"body": "ሰውነታቸውን በእርሻ ላይ ከሚወድቀው ጉድፍ ጋር በማነጻጸር የሚሞተውን በጣም ብዙ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “የእንስሳት አዛባ በየሜዳው እንደሚወድቅ እንደዚሁ የሰዎች ሬሳ በየቦታው ይወድቃል” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ከአጫጆች በኋላ እንደሚቀር ቃርሚያ ",
"body": "ይህ ሰውነታቸውን ከአጫጆች በኋላ ከሚቀረው ቃርሚያ ጋር በማነጻጸር የሚሞተውን በጣም ብዙ ቁጥር ያለውን ሕዝብ ይገልጻል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ገበሬዎች ሰብላቸውን ካጨዱ በኋላ በየቦታው ወድቆ እንደሚቀር ቃርሚያ” (ተነፃፃሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "እነርሱን ለመሰብሰብ አንድም ሰው አይኖርም",
"body": "“የሞቱትን ሰዎች ሬሳ ለመሰብሰብ አንድም ሰው አይኖርም” "
}
]