am_jer_tn/09/10.txt

54 lines
4.8 KiB
Plaintext

[
{
"title": "አጠቃላይ መረጃ፡- ",
"body": "እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ሕዝብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡ በቁጥር 12 ኤርምያስ አስተያየት ይሰጣል፡፡"
},
{
"title": "እኔ የሃዘን ልቅሶ አለቅሳለሁ … ለማሰማርያዎቹ የቀብር ልቅሶ ይለቀሳል",
"body": "የሞተች ሰው እንደሆነች በማሰብ እንደዚሁ እግዚአብሔር ለእስራኤል ምድር ያለቅሳል፡፡ (ትይዩነት/ተመሳሳይነት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የቀብር ልቅሶ ይለቀሳል",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እኔ የቀብር ልቅሶ አለቅሳለሁ” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ማሰማሪያዎቹ",
"body": "“እንስሳት ሳር የሚግጡበት የግጦሽ ስፍራ”"
},
{
"title": "እነርሱ ተቃጥለዋልና",
"body": "ይህ በገቢር ቅርጽ ሊብራራ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምክንያቱም ሰው ማሰማሪያዎቹንና የግጦሽ መሬቱን አቃጥሎአቸዋልና” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የአንድም ከብት ድምጽ ፈጽመው አይሰሙም",
"body": "“በዚያ ስፍራ አንድም ሰው የከብት ድምጽ አይሰማም”"
},
{
"title": "የቀበሮ መሸሸጊያ",
"body": "“ቀበሮዎች የሚደበቁበት ስፍራ፡፡” ቀበሮዎች እጅግ በጣም ኃይለኛ የዱር ውሾች ናቸው፡፡"
},
{
"title": "ሰው የማይኖርበት ስፍራ",
"body": "“አንድም ሰው የማይገኝበት ስፍራ”"
},
{
"title": "ይህን የሚያስተውል ጠቢብ ሰው ማን ነው?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ የተናገራቸውን ነገሮች መረዳት የሚችል ሰው በጣም ጥበበኛ ሰው ብቻ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ነገሮች መረዳት የሚችሉ በጣም ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ያወራስ ዘንድ የእግዚአብሔር አፍ ለማን ተናገረ",
"body": "እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው እነዚህን ነገሮች መናገር የሚችሉት እርሱ የተናገራቸው ሰዎች ብቻ እንደሆኑ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እነዚህን ነገሮች ለሌሎች ማብራራት የሚችሉት ከእግዚአብሔር የተማሩ ብቻ ናቸው” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "የእግዚአብሔር አፍ ",
"body": "እዚህ ላይ የእግዚአብሔር ንግግር በእርሱ “አፍ” ተወክሏል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “እግዚአብሔር” (ወካይ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)"
},
{
"title": "ሰው እንዳያልፍባት ምድሪቱ ለምን ጠፋች፣ ለምንስ ወና ሆነች?",
"body": "እግዚአብሔር ይህን መልስ የማይሰጥበት ጥያቄ የተጠቀመው ምድሪቱ ለምን እንደጠፋች ማብራራት የሚችለው ጥበበኛ ሰው ብቻ እንደሆነ አጽንዖት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ሰው እንዳያልፍባት ምድሪቱ ለምን እንደጠፋች እና ወና እንደሆነች ማብራራት የሚችለው ጥበበኛ ሰው ብቻ ነው፡፡” (መልስ የማይሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚለውን ይመልከቱ )"
},
{
"title": "ምድሪቱ ጠፍታለች ደግሞም ወና ሆናለች",
"body": "ይህ እንደ ዓረፍተ ሃሳብ ሊጻፍ ይችላል፡፡ “ጠፋች” እና “ወና ሆነች” የሚሉት ሁለቱም ምድሪቱ ወና እንደሆነች የሚያብራሩ ናቸው፡፡ አማራጭ ትርጉም፡- “ምድሪቱ ወና ሆናለች” (ገቢር/አድራጊ ወይም ተገብሮ/ተሳቢ እና ጥምር ቃል የሚለውን ይመልከቱ)"
}
]